newz2

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ጉበኝት አደረጉ ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ጉበኝት አደረጉ ::

በዛሬም የመስክ ጉበኝት የቢሮ አመራሩ ከቦርጃ ውጅግራ ፕሮጀክት የ5.56 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን የፕሮጀክት ስራዎች ያለበትን ለማየት ተችሏል:: በጉብኝቱም የመንገዱ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለማየት ችለናል::

የመንገዱ መገንባት የማልጋ እና የወንዶ ገነት ወረዳን የሚያገናኝ በመሆኑ ለአከባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እጅግ በጣም ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መንገድ እንደሆነ በምልከታ ወቅት ለማረጋገጥ ችለናል::

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ዉስጥ እስከ ጥር 30/04/2016 ዓ. ም ድረስ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ የእስታር የሥራ ተቋራጩ አስተባባሪዎች አሳውቋል:: ፕሮጀክቱ በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቅ የቢሮ ማናጅመንት አመራሩ በቅርበት ክትትል እንደሚያደርጉ ገልፃዋል::

ታህሣስ 18፣ 2016 ዓ. ም 

ሐዋሳ, ሲዳማ

newss4444

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ በሰሜን ሲዳማ ዞን በለኩ ከተማ አስተዳደር በራማዳ ቀበሌ አቅም ለሌላቸዉ ቤተሰብ የቤት ግንንባታ ማስጀመሪያ ተካሄደ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ በሰሜን ሲዳማ ዞን በለኩ ከተማ አስተዳደር በራማዳ ቀበሌ አቅም ለሌላቸዉ ቤተሰብ የቤት ግንንባታ ማስጀመሪያ ተካሄደ::

በፕሮግራሙም የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች የሰሜን ሲዳማ ዞን አመራር እንዲሁም የለኩ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት ለአንዲት አቅመ ደካማ እና 4 ልጆች ላሏት እናት ግንባታ የማስጀመር ስራ ተጀምሯል ::

ይሄ ተግባር የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች በራሳቸው ተነሳሽነት እና ፍላጎት ገንዘብ በማዋጣት ያስጀመሩት እንደሆነ ተገልጿል::

በመቀጠልም በለኩ ከተማ አስተዳደር የመናሃሪያ ግቢ ዉስጥ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መሪሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በቀጣይ መከታተል እና መንከባከብ ከሁሉም የሚጠበቅ እንደሆነ የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አስገንዝቧል::

የሰሜን ሲዳማ ዞን ተወካይ በበኩላቸዉ የሲዳማ ህዝብ ያለው ለሌለዉ የማካፈል የባህል እሴት ያለው መሆኑን ጠቅሶ ይሄን ተግባር በቢሮ ደረጃ ማከናወን በመቻሉ በዞኑ ስም ምስጋናቸዉን አቅርቧል::

በሌላም በኩል የለኩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፀጋዬ አባቴ መዕልክታቸዉን ሲያስተላልፉ ደሃን እና አቅም የሌላቸዉን መርዳት ፈጣሪ የምደሰትብን ተግባር በመሆኑ በቀጣይ መሰል ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል::

በመቀጠልም ከበጎ ተግባር ጎን ለጎን በለኩ ከተማ አስተዳደር ስለ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን ግ ንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል::

ሐዋሳ, ሲዳማ
መስከረም 10፣ 2016 ዓ.ም.

 

slide19

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ሥራ በሲዳማ ክልል በይፋ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ሥራ በሲዳማ ክልል በይፋ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

news84

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ከከልሉ ፖሊስ ኮሚሸንና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከፌዴራል የትራንስፖርትና ሎጂስትክስ ሚኒስቴር ከመደህን ፈንድ እና መንገድ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባባር የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላኪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቁጥጥር ሥራ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ድንገተኛ የቁጥጥር ተግባሩ ለተከታታይ 25 ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

መስከረም 4/2016 ዓ.ም ሃዋሳ፣ ሲዳማ

news 55

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመልካም አስተዳደርና የካይዘን አተገባበርን በተመለከተ ለቢሮ ሠራተኞች ስልጠና ለመስጠት እና የ2016 ዓ.ም እቅድ ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ ተግባቦት ለመፍጠር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሄደ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመልካም አስተዳደርና የካይዘን አተገባበርን በተመለከተ ለቢሮ ሠራተኞች ስልጠና ለመስጠት እና የ2016 ዓ.ም እቅድ ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ ተግባቦት ለመፍጠር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሄደ::

በስልጠና እና በውይይት መድረክ ላይ የማናጅመንት አባላት እና አጠቃላይ የቢሮ ሰራተኞች በተገኙበት እየተካሄደ ያለ ሲሆን የተዘጋጀዉ ሰነድ በመልካም አስተዳደር የማስፈን ጉዳዮች እና በካይዘን ስራዎች አተገባበር ዙሪያ ከክልሉ ፓብልክ ሰርቪስ እና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ የመጡ ከፍተኛ ባለ እየሰጡ ይገኛሉ::
 
በመቀጠልም የቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርቦ በቢሮ ሰራተኞች ጋር ተግባቦት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል::
…………………………………..
 
ጳጉሜ,3/2015 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
new123

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጳጉሜ 1 የአገልግሎት ቀን በክልል ደረጃ በሁሉም መናሃሪያዎች ዉስጥ ተከበረ::

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጳጉሜ 1 የአገልግሎት ቀን በክልል ደረጃ በሁሉም መናሃሪያዎች ዉስጥ ተከበረ::

በመረሃ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል የሪኦተ ዓለም እና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አስፋው ጎኔሶ እንዲሁም የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንትባ ክቡር መኩሪያ ማርሻዬ እንዲሁም የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት የትራንስፖርት ማህበራት ተሳፋሪዎች እና አሽከርካሪዎች በተገኙበት የጳጉሜ 1 ቀን የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በክልል ደረጃ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በአሮጌ መናሃሪያ እየተበረ በሚገኘው ፕሮግራም ላይ የታክስ አግልግሎት ከ12 ሰዓት ጀምሮ ነፃ እንደሆነ እና ሁሉም ተሽከርካሪ በጥንቃቄ አገልግሎት እንዲሰጡ እና በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰዉን ሞት በጋራ ሁሉም የባለ ድርሻ አካላት መከላከል እንደሚገባ የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አስፋው ጎኔሶ ግልፆዋል ::
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በበኩላቸዉ በዛሬ ዕለት ሁሉም አሽከርካሪዎች የሚሰጡትን አገልግሎት ህዝብን ባማከለ እና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል::
በእለቱ አሽከርካሪዎች, የማስልጠኛ ተቋማት የህግ አስከባሪዎች እንዲሁም ተሳፋሪዎች ቃል መሃላ በመግባት ማጠቃለያ ተደርጓል::
ጳጉሜ 1/2015 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
news 1

የ9 ወር የተግባር አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ ::

የ9 ወር የተግባር አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ9 ወር የተግባር አፈፃፀም ግምገማ እና በቀጣይ የሚሰሩ ሰራዎች ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የተዘጋጀ የግምገማ መድረክ ተደረገ::

በግምገማ መድረኩም የተግባር አፈፃፀም እና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚተገበሩ ጉዳዮችን የያዘ ሰነድ ቀርቦ የቢሮ አመራር እና አጠቃላይ ባለሙያዎች በተገኙበት በዝርዝር ተገምግሞ ለቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል::

news 23

የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ድንገተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ።

የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ድንገተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ።

በሲዳማ በሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጅስትክ ሚኒስቴር የመድህን ፈንድና የመንገድ ደህንነት አገልግሎት ባለሙያዎች እንዲሁም የፌደራል ፖልሲ ኮሚሽን ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ድንገተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ።

መጋቢት 1/2015 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ፣ በቱላ ክ/ከተማ ፣ እንዲሁም ከሀዌላ ወረዳ እስከ ሸበድኖ ወረዳ ሞሮቾ ከተማ ድረስ የትራፊክ አደጋ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫና ድንገተኛ ቁጥጥር ሥራ በሁለተኛ ቀን ፕሮግራም ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የዚህ የድንገተኛ የተቀናጀ ቁጥጥር ዋና አላማው አሽከርካሪዎች ከመጠን በላይ እንዳያሽከረክሩ፣ ከወንበር ቁጥር በላይ ትርፍ ሰዉ እንዳይጭኑ ትምህርት በመሰጠትና ደንብ ተላልፎ የተገኙ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ::

በሌላም በኩል በድንገተኛ ቁጥጥር ወቅት ሰሌዳ, ቦሎ ፣የሦስተኛው ወገን ፣ የብቃት ማረጋገጫና በሌሎች ጉዳዩች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን የጀመረው የተቀናጀ የቁጥጥር የሁሉም በሲዳማ ክልል ውስጥ ባሉት ወረዳዎች ላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ታዉቋል ::

…………………………………………….

news 31

በዩራፕ ዘርፍ በተደራጁ በወጣቶች አደረጃጀት 27 ፕሮጀክቶች ጥገና እንደሚደረግ ተገለፀ::

በዩራፕ ዘርፍ በተደራጁ በወጣቶች አደረጃጀት 27 ፕሮጀክቶች ጥገና እንደሚደረግ ተገለፀ::

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ በዩራፕ ዘርፍ በተደራጁ በወጣቶች አደረጃጀት 27 ፕሮጀክቶች ጥገና እንደሚደረግ ተገለፀ::

በባልፈው በጀት ዓመት በፕሮጅክት ሥራ አፈፃፀም ግምገማ መነሻ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ያመጡት ከ72 ማህበራት ዉስጥ 56 ማህበራት ተለይቶ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተጠቅሷል ::

በተመረጡና የሥራ ዕድል በተፈጠረላቸዉ ወጣቶች በኩል 195.5 ኪሜ መንገድ በ14 ወረዳዎች ጥገና እንደሚደረግ ታውቋል ::

በመጨረሻም ማህበራቱ የሚሰሩትን መንገዶችን በዕጣ እንዲለዩ ተደርጎ የዕለቱ ፕሮግራም ማጠቃለያ ተደርጓል::