newz 1010

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የ2017 ዓ.ም ሀገራዊ የተቀናጀ ድንገተኛ የቁጥጥርና ግንዛቤ ሥራ  ከፌዴራል መንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከሲዳማ ክልል  ጠቅላይ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም ከሀዋሳ ከተማ አስተዳዳር ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል ::

የቁጥጥር  ሥራ በተመረጠው የቁጥጥር ቱላ ክፍለ ከተማ ገመጦ ወንዶ ገነት መታጠፊያ  አከባቢ፤ እንዲሁም ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ጨኮ ወረዳና ከተማ አስተዳደርና ዳራ ቀባዶ ወረዳ መጪሾ አከባቢ  መስመር  ከሁለቱም ዞን፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት  ጎልተው የታዩ ደንብ መተላለፊያዎች ላይ ቁጥጥር ተደርጓል ::

በተደረገው የተቀናጀ ቁጥጥር ወቅት የደህንነት ቀበቶ አለማሰር፣ የቴክኒክ ምርመራ ቦሎ አለማደስ፣ 3ኛ ወገን አለመግባት፣ ትርፍ ተሳፋሪ መጫን፣ ያልተፈቀደ እስቲከር መለጠፍ፣ ያለ መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር እንዲሁም በተለያዩ ደንብ መተላለፎች ላይ ያተኮረ የቁጥጥር ሥራ ተሰርቷል::

በዕለቱ በተሰራው የቁጥጥር ሥራ  በአጠቃላይ 431 ተሽከርካሪዎች የታዩ   ሲሆን፡  ከነዚህ ውስጥ ደንብ ተላልፈው የተገኙ 56 አሽከርካሪዎች  ላይ  ተገቢው የህግ ማስከበር እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ታውቋል:: ከደንብ ተላላፊዎች  ብር 57,500 (ሃምሳ ሰባት ሺ  አምስት መቶ  ብር) ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ወቅት የተወሰነ ክፍተት ያለባቸው አሽከርካሪዎች 375 የሚሆኑት በቀጣይ እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት 850 ለሚሆኑ ተሳፋሪዎችና ለ100 ባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል:: የተቀናጀው ቡድን የቁጥጥር ሥራ በቀሪ ቀናት በተለዩ ቦታዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

24/03/2017 ዓ.ም

ሐዋሳ፥ ሲዳማ

newz 1001

በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::

በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::

ከፌዴራል መንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ከመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ የተውጣጣ ግብረ ሀይል የድጋፍና ቁጥጥር ሥምሪት እንደተሰጠው ተመላከተ።

የድጋፍና ቁጥጥር ተልዕኮው የሚተገበረው በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማና በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ሲሆን ለ12 ቀናት እንደሚቆይም ተብራርቷል።

የቢሮ ሀላፊው አቶ ታምሩ ታፌ ሥምሪቱን ለግብረ- ሀይሉ ሲሰጡ በንግግራቸው:- ተልዕኳችሁ በዋናነት በመናኽሪያዎች አካባቢ የሚካሄድ የህግና ደንብ ትግበራ በተጨማሪም በእንቅስቃሴ ወቅት አሽከርካሪዎች ደንብና ህግ ጠብቀው ስለመንቀሳቀሳቸው ትኩረት ሠጥተው እንዲሰሩ  አስገንዝበዋል።

አክለውም ተልዕኳችሁ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ተቋማችን ከጎናችሁ ነው ሲሉ አብሮነታቸውን አረጋግጠዋል።

ለተቀናጀ ቁጥጥር ሥራ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲንቀሳቀሱ እና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስቧል::

የከተማ ታክሲ ታሪፍ ጥናት ተሰርቶ በሀዋሳ እና በክልል ከተሞች ተግባራዊ እንዲደረግ በቢሮ በኩል የወረዳውን ተግባራዊነቱ በግብረ ኃይሉ በኩል በትኩረት ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ ጨምሮ አስገንዝቧል::

18/03/2017 ዓ.ም.

ሐዋሳ ሲዳማ

newz001

በመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ለመንግስት ሰራተኞች “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

በመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ለመንግስት ሰራተኞች "የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ እንደገለፁት ስልጠናው በሀገር ደረጃ የሚሰጥ እንደመሆኑ ሰራተኞች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በሀገር ደረጃ እየተሰሩ ያሉትን ሥራዎች እና ቀጣይ የሚተገበሩ ጉዳዮችን በአግባቡ መገንዘብ ይገባል ብለዋል ::

የሰለጠነ የሰው ህይልን በመገንባት ቀልጣፋ እና ዉጤታማ ሥራ እንዲሰሩ ለማድረግ በቀጣይም ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል::

ለስልጠናው መድረክ የተዘጋጀ ሠነድ በንባብ የቀረበ ሲሆን ስልጠናው ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ታውቋል ::

ህዳር 2/2017 ዓ.ም. ፣ ሐዋሳ

bhead

ተቀናጅቶ መሥራት ለሴክተር ሥራ መሳካት ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ::

ተቀናጅቶ መሥራት ለሴክተር ሥራ መሳካት ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ::

bhead

በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ ተካሂዷል::

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ አስፋው ጎኔሶ እንደገለፁት ይህ ሴክተር ለሲዳማ ሕዝብ የመልማት ቁጥር አንድ አጀንዳ የሆነውን የመንገድ የልማት ሥራን የሚሰራ ተቋም በመሆኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል::

የመንገድ እና የድልድይ ግንባታ ተደራሽነት እንደ ጥሩ የሚታይ ቢሆንም ከጥራት ጋር ተያይዞ ለሚታዩ ችግሮች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ተገልጿል::

በሌላም በኩል የትራንስፖርት ዘርፍ አከባቢ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ የሕዝቡን እንግልት ማስቀረት እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራዎችን ሪፎርም በማድረግ የሚታዩ ችግሮች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይገባል በማለት ተናግሯል::

በመክፈቻው ወቅት የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እንደተናገሩት በቢሮ ደረጃ በመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራዎች በበጀት ዓመቱ ዉጤታማ እንደነበረ ተናግረዋል::

በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ዘርፍም በተሰራው ሥራ የሞት መጠን የቀነሰ ቢሆንም  በሰው እና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ማስቆም እስካልቻልን ድረስ በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ ተጠቅሷል::

በክልል ደረጃ በ2016 በጀት ዓመት 107  የሞት አደጋ መከሰቱንና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እና የአካል ጉዳት የደረሰ በመሆኑ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በሙሉ  በመቀናጀት የአደጋ መንስኤን በመለየት መስራትና መከላከል እንደሚገባ ተገልጿል::

በሴክተር ጉባኤው ለዉይይት መነሻ የሆኑ ሰነዶች የ2016 በጀት ዓመት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድን የቢሮው የልማት እቅድ በጀት ክትትል ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ወገኔ ታምራት ያቀረቡ ሲሆን የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የንቅናቄ ሠነድን ኮሮኔል ሮዳሞ ኪአ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ዘርፍ ኃላፊ አቅርበው ውይይት ተደርጓል::

rd

የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል እና አደጋዉን ለመቀነስ ሁሉም የባለድርሻ ተቋማት እና አካላት በመቀናጀት ከሰሩ የንቅናቄ ሠነዱን ሲያቀርቡ ኮሮኔል ሮዳሞ ኪአ ተናግረዋል::

በመድረኩም የተሻሻለው የትራፊክ ቅጣት ደንብ እና በአደጋ ወቅት የመጀመሪያ ሕክምና ክፍያ ማሻሽያ የተደረገውን ደንብ እስከታች በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በቀረበው ሠነድ ተብራርቷል::

በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ላይ ከተሳታፊ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥተው በቀጣይ በሴከተር ደረጃ በቅንጅት በመስራት የተጣሉ ግቦችን ማሳካት አስፈላግ መሆኑን ገልፆዎ ከዞኖች እና ከሐዋሳ ከተማ አስተዳር ጋር በቀጣይ በምሰሩ አቅጣጫዎች ላይ የግቢ ስምምነት ተደርጎ የሴክተር ጉባኤ መድረክ ማጠቃለያ ተደርጓል::

በመድረኩም የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አስፋው ጎኔሶ፣የቢሮ ኃላፊ ክቡር ታምሩ ታፌ፣ የፕሬዘደንቱ የመሰረተ ልማት አማካሪ ክቡር ዘገዬ ሀሜሶ፣ ክብርት ምንትዋብ ገ/መስቀል የከተማ እና መሰረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የዞንና የሐዋሳ ከተማ አመራሮች፣የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የባለድርሻ አካላት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::

   =======================

መስከረም, 2017 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

rod

ወቅቱን የጠበቀ የሙያ ላይ ሥልጠና ግንዛቤን የማሳደግ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ወቅቱን የጠበቀ የሙያ ላይ ሥልጠና ግንዛቤን የማሳደግ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

rod

ይህ የተገለፀዉ ለአሽከርካሪዎች በሥነ- ምግባር፣ አዲስ በተሻሻሉ የመንገድ ደህንነት ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም የመድህን ፈንድ አዋጆችን ለማሳወቅ በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ነው።

በመድረኩ በርካታ አሽከርካሪዎች፣ የትራፊክ ፖሊስ አባላት፣ የክልልና መምሪያ አመራርና ባለሙያዎች  ተሣታፊ ሆነዋል።

road safety 2
road safety 3

የቢሮ ሀላፊ ተወካይና የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ ኮ/ ሮዳሞ ኪአ በመልዕክታቸው እንደገለፁት የዛሬው መድረክ ዓላማ አሽከርካሪዎች የተከበረ ሙያ ያላችሁ የተከበረውን የሰው ልጅን ህይወት ይዛችሁ የምትንቀሳቀሱ፣ በስነምግባር የታነፃችሁና አዳዲስ ከወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር እንድትተዋወቁ ታሳቢ በማድረግ ነው።

 አክለዉም ባለፈው ዓመት በተከሰተው የትራፊክ አደጋ ዋናው መንስዔ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑን ገልፀው በዝግታና በእርጋታ እንድታሽከረክሩ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሰነዶች ቀርበው በሳል ሙያዊ ገለፃ ተደርጎባቸዋል።

road safety

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አዳነ አየለና የክልሉ መንገድ ደህ/አቅ/ግን/ድህ /አደ/መድህን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዶካ ከመድረክ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተውባቸው መግባባት ላይ ተደርሶ  መድረኩ ተጠናቋል።

 “በትራፊክ አደጋ አንድም ህይወት እንዳይጠፋ፣ አካል እንዳይጎድል፣ ንብረት እንዳይወድም ሁላችንም ሀላፊነት አለብን! “

 መስከረም 2017 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

nez1

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላክያ የአብይ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላክያ የአብይ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ::

በመድረኩም የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር በየነ ባራሳ, የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ የኮሚቴ አባላት የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::

በመድረኩም አጠቃላይ ክልላዊ የትራፊክ አደጋ መከላክያ የመነሻ ሠነድ በቢሮ ኃላፊ በአቶ ታምሩ ታፌ ቀርቦ የመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት በማድረግ በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ በማንሳት ሁሉም እንደ ተቋማቸው ወስደው የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ ገልፀዋል::

በተጨማሪም በክልል ደረጃ እንዲሁም በሁሉም ዞኖች እንዲሁም በወረዳዎች የግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስቷል::

የትራፊክ አደጋ እንዴ ሀገር እያደረሰ ያለዉን ዘርፈ ብዙ ጉዳትን ለመቀነስ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ እንዲሰሩ ለማድረግ ታቅዶ የተዘጋጀ መድረክ ሲሆን በአስከፍው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የሞት የአካል ጉዳት እንዲሁም በእኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ እያደረሰ ያለውን ቀውስን ለመቀነስ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ተገልፆዋል::

በመጨረሻም ክቡር ምክትል ፕረዝደንት እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በቀጣይ ከኮሚቴ ምስረ ታ ጀምሮ በክልል ደረጃ በሚሰሩ ስራዎች ላይ በቅርበት በቅንጅት በመሥራት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ የድርሻቸውን እንዲወጡ እና ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል::

ሰኔ 03/2016 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ

newz199

ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች የመጀመሪያውን ክልላዊ የሴክተር መ/ቤቶች ዉድድር አሸናፊ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ::

ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች የመጀመሪያውን ክልላዊ የሴክተር መ/ቤቶች ዉድድር አሸናፊ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ::

ኮከቦቹ በሀዋሳ ሰማይ ላይ ደመቁ::

የተቋማችንን ተልዕኮ ለማሳለጥና የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ በጋራ ለጋራ ስኬት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በአጠረ ጊዜ ዉስጥ በመገንባት በመንግሥት ተቋማት የእግር ኳስ የስፖርት ዉድድር ላይ ገና ከጅማሬዉ በሁለቱም ፆታ ያስመዘገብነዉ  ቻምፒዮንነት/ አሸናፊነት የዉስጥ የሴክተራችንን ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችንን ለይተን ጥንካሬያችንን ይበልጥ አጎልብተን ጉድለታችንን በፍጥነት አርመንና አካክሰን ለመሥፈንጠር ለጀመርነዉ ጉዞ የትክክለኛ እርምጃ  ማሳያ ዉጤት መሆኑን የተረዳንበት ሕያዉ ምስክር ነዉ።

በመሆኑም ይኸንን ድል በቀጣይ ሁሉም ዘርፎቻችን:ዳይሬክቶሬቶቻችን: ባለሙያዎቻችንና መላዉ መዋቅራችን በተሰጠን ቦታ ከተባበርን ከተደጋገፍን ከተቀናጀን ግልፀኝነትን ፈጥረን ሌብነትና ብልሹ አሠራር በተግባር ተፀይፈን ሕባችንን በፍትሃዊነትና በቅንነት በተሰጠን ጊዜ አገልግለን ዕርካታዉን ካረጋገጥን ሥራችንን በግልፅ መዝኖ የሚገባንን ዉጤት በሚሰጠንና በሚከፍለን እግ/ር: መንግሥት:ፓርቲና ሕዝባችን ፊት ገንዘብ ሊገዛዉ በማይችል ዋጋ የሚተመነዉን ምስክርነትና ሽልማት በአደባባይ ከመቀበል የሚበልጥ ክብርና ዕርካታ ምን አለ? የሴክተራችን ዕንቁና ተወዳጅ የሆናችሁ የማከብራችሁ ባልደረቦቼና  ቤተሰቦቼ ።

ስለዚህ ይህንን አዉቀን በቀሪ ጊዜያችን የአምላካችን የእግ/ር  ዕገዛና ብርታት ፀጋዉን ከሁሉም በላይ አብሮነቱ ጥበቃዉ በዝቶልን ከሚሰጠን ሰላምና አንድነት የሚመነጭ ፍቅር እና ርህራሄ ተላብሰን በዓላማ አንድነት ተጋምደን የሚጠበቅብንን የላቀ ዉጤት አስመዝግበን ለበለጠ ሽልማት እንድንነሳ አደራ እያልኩ ዉድና ዕንቁ የሆናችሁ ተጫዋቾቻችንና የሴክተራችን ሠራተኞች እንዲሁም መላዉ የስፖርቱ ቤተሰቦች ለድካማችሁ ድሉ ስለሚገባችሁ ኮርተንባችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን እላለሁ።

በመጨረሻም ፍፃሜያችን በድል ዋንጫ ታጅቦ በሀዋሳ ሰማይ ላይ ደስታችሁ እንደደመቀ በተሰማራችሁበት ሁሉ ጅማሬያችሁ ሂደታችሁና ፍፃሜያችሁ በአንድነት ለጋራ ድል በጠንካራ ቲሞ ስፕሪት በደስታ በስኬት በፍቅር በዉጤት በድርብ ድል የደመቀ ይሁንላችሁ ።

ብሩህ ጊዜ!

መጋቢት 22/2016 ዓ.ም.

ሐዋሳ, ሲዳማ

newz112

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ከመጋቢት 09 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለፀ::

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ከመጋቢት 09 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለፀ::

በመንገድ የትራፊከ አደጋ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለመቀነስ የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በሲዳማ ክልል ከመጋቢት 09 -መጋቢት እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ታምሩ ታፌ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ታምሩ ታፌ እንደተናገሩት በህጉ ዙሪያ ለተቆጣጣሪ አካላት እና ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር በማስተባበር፣በመደገፍ፣ በመከታተልና በመገምገም ህግ የማስከበር ስራው ተጠያቂነት ባለው መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ፤በሞተር ሳይክል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ስራ ማከናወን ፣ከክልል የዞንና ወረዳ ኃላፊዎች፣ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ፣ከትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እና በዋናነት ይህን አስከፊ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መቀነስ እንደሆነ በመግለጫቸው ገልፀዋል፡፡

የተቀናጀው የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስተባባሪነት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ ጋር በቅንጅት የሚሰራ ይሆናል፡፡

በፕሮግራሙም መሰረት ለአሽከርካሪዎች እና ለተማሪ ትራፊክ ክበብ ኮሚቴዎች የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሐዋሳ ከተማ, በይርጋአለም ከተማ እንዲሁም በአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር እንደሚሰጥ በመግለጫ ወቅት ተገልፆዋል::

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በሲዳማ ክልል ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እስከ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ዳዬ ድረስ በተመረጡ መስመሮች ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

መጋቢት 08/2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ