በሲዳማ ክልል የዩራፕ ፕሮጀክቶች ዋጋ ማሻሻያ ጥናት ላይ ምክክር ተደረገ::
በሲዳማ ክልል በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸው በሚከናወኑ የመንገድ እና የድልድይ ግንባታዎች የዋጋ ማሻሻያ ጥናት ቀርቦ ምክክር ተደረገ ::
በምክክር መድረኩ በጥናት ቡዱኑ ኮሚቴ አባላት በክልል ደረጃ ዋጋ ማሻሻያ ለማድረግ መሰረታዊ ምክንያት የሆኑ ጉድዮች ተለይቶ ጥናት እንደተደረገ ከቀረበዉ የጥናት ሠነድ ለማረጋገጥ ተችሏል::
በመድረኩ ተገኝተው የጥናቱን አስፈላጊነት በክልል ደረጃ ከክልሉ መንግስት ምክር ቤት አባላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አባላት በተገኙበት ምክክር በማድረግ ፀድቆ በሥራ ላይ እንዲዉል ለማድረግ እንደሆነ የርዕሰ መስተዳደሩ ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ ተናግረዋል::
በክልል ደረጃ በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸዉ የሚከናውኑ ድልድዮች፥ የመንገድ ጥገና እና ግንባታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ በየጊዜው የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ጥራት ያለው ሥራ እንዲሰራ ለማድረግ እንደሆነ ከቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና በኩል ተገልጿል::
የዋጋ ማሻሻያን በተመለከት በሀገር ደረጃ የግንባታ እቃዎች ዋጋ መጨመር፣ የጥገና ዋጋ መጨመር፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፣ እንዲሁም የሠራተኞች ክፍያ እንደ ምክንያት የተለዩ ጉዳዮች እንደሆነ ከቀረበው የጥናት ሠነድ ተመላክቷል::
በቢሮ በኩል የተደራጀዉ የጥናት ቡድን ከ ሲዳማ ክልል የኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኩል ተገምግሞ የዳበረ ሲሆን በቀረበዉ መነሻ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ተጨማሪ መደረግ የሚገባቸዉ ጉዳዮች ተለይቶ እንዲቀርብ በመድረኩ የተገኙት የካቢኔ አባላት ተናግረዋል::
የሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ የሚጀመሩ ፕሮጀክቶች በጥራት እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባ ከመድረኩ ተገልጿል::
የጥናቱ ሥራ በተያዘለት ጊዜ ዉስጥ እንዲጠናቀቅ የመንገድ ልማትና ትራስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት ወቅታዊ የዋጋ ሁኔታን መነሻ በማድረግ ጥናቱን አጠናቆ እንዲያቀርቡ እና ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል::
በመድረኩ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ፣ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና፣ የካቢኔ አባላት፣ የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች፣ የኮንስትራክሽ ባለስልጣን ኃላፊ እንዲሁም ጥናት ቡዱን አባላት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ህዳር 17/2018 ዓ.ም.




