newz49

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጥና የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጥና የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

ከክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ፤ከክልሉ ጠቅላይ  ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም በየደረጃው ካሉ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በክልላችን በተመረጡ ቦታዎች በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአሮጌው መናኸሪያ ውስጥ :- የሶስተኛ ወገን፣ የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ቦሎ፣ የስምሪት ሂደት ፣የተሳፋሪ የትኬት አቆራረጥና መውጫ አሰጣጥን አስመልከቶ እንዲሁም በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ መናኸሪያ ዉስጥ ቁጥጥር ተደርጓል:: የቁጥጥርና የተቀናጀ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን በቁጥጥር ወቅት ጎልተው የታዩ ደንብ ተላላፊዎች በህጉና በደንቡ መሠረት ተገቢው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ፡፡ 

የተቀናጀውን የቁጥጥር ቡድን በየደረጃው ሥራውን  ያለበት ሂደትና ያጋጠሙ ችግሮችን ከሁለቱም መዋቅር ጋር በመሆን ጎን ለጎን በመገምገም በቦታው እየተፈታ መሄድ እንዳለበትና  የቁጥጥር ተግባሩ አጠናክሮ በማስቀጠል የህግ ማስከበርና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል ።

የተቀናጀው የቁጥጥር ቡድን በቀጣይም በሌሎችም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚቀጥል ይሆናል ።

የካቲት 11 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

bheadz2

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የቢሮው ስፖርት ቡድን የፋይናንስ አቻውን በማሸነፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ ::

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የቢሮው ስፖርት ቡድን የፋይናንስ አቻውን በማሸነፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ ::

የቢሮአችን ዕንቁዎች ዋጋችዉ በምንም የማይተመን ብርቅዬዎች ናችሁና ገና ከመነሻዉ በስፖርቱ ያስመዘገባችሁትን ድል በቀጣይም እስከፍፃሜዉ አስጠብቃችሁ ብቻ ሳይሆን የበለጠ እያስመዘገባችሁ እንደምትቀጥሉ እምነቴ ፅኑ ነዉ።

በስፖርቱ የተጀመረው ስኬታማነት በመንገድ ልማት፣ በትራንፖርት ዘርፍ፣ በመንገድ ደህንነትና በሰዉ ተኮር/ በጎ አገልግሎት ሥራዎቻችን ላይ የቢሮአችንን ተልዕኮ ማሳካት ብቻ ሳይሆን የልህቀት ማዕከል አድርገን ማየት ብለን ያስቀመጥነዉን ግብ ተባብረንና ተደጋግፈን የቡድን መንፈስ/team spirit/ ገንብተን ሕዝባችንን ዝቅ ብለን በማገልገል የተገልጋዮቻችንን ዕርካታ በማረጋገጥ ራዕያችንን ዕዉን እንደምናደርግ ለገባነዉ ቃል ኪዳን የማሳኪያ ማሳያ ዉጤት ስለሆነ እንኳን ደስ አለን።

የቀድሞ ቢሮዬ ባልደረቦቼ ሽንፈት መዉደቂያ ሳይሆን ለቀጣይ ስኬት ጉድለትን በመለየት የመፍትሄ አማራጭ በመፈተሽ የድል መንደርደርያ መንገድ ነዉና አይዟችሁ።

 ድልና ድምቀት ለጋራ ራዕያችን ለሁላችን ይሁን ።

newz94

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማጠቃለያ ተደረገ::

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማጠቃለያ ተደረገ::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ኃላፊ፣ ክቡር አቶ ዘገዬ ሀመሶ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ፣ የዞን ዋና አስተዳደሪዎ እና የፊት አመራሮች፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተደርጓል::

በሴክተር ጉባኤው ላይ የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሠነድ እንዲሁም የባለ ሁለት ጎማ ሞተር አደረጃጀት መመሪያ የጉባኤ አጀንዳዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጉባኤው ተሳታፊዎችም በቢሮ ደረጃ እስከ ታች እየተከናውኑ ያሉትን ተጨባጭ ለዉጥ እያስመዘገቡ የሚገኙ እንደሆነ አንስተው በተለይ ከመንገድ ልማት ሥራዎች አንፃር ከጥራት ጋር ተያይዞና በጊዜ ከማጠናቀቅ አንፃር ትኩረት ይበልጥ እንዲደረግ ተነስቷል::

በሌላም በኩል በመንገድ የትራፊክ አደጋ መከላከል ረገድ እየመጡ ያሉትን ለዉጦችን በማጠናከር የትራፊክ አደጋ እያስከተለ የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ በመቀናጀ መቀነስ እንደሚገባ ተገልፆዋል::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ በተነሱ ሃሳቦች ላይ ምላሽ በመስጠት በ ጋራ በመቀናጅት መሥራት ከቻልን በመጨረሻም የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልፆዎ በእለቱም ለሴክተር ጉባኤ መሳካት የራሳቸውን ሚና ለተወጡ አካላት የምስጋና እዉቅና ሰርትፊኬት ተሰጥተዉ የእለቱ መድረክ ማጠቃለያ ተደርጓል::

ጥር 17/2016 ዓ.ም

newz91

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ተጀመረ::

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ተጀመረ::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ኃላፊ ፣ ክቡር አቶ ዘገዬ ሀመሶ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ፣ የዞን ዋና አስተዳደሪዎች እና የፊት አመራሮች፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳና አስተዳዳሪዎች፣ የፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል::

በሴክተር ጉባኤው ላይ የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት፥ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሠነድ እንዲሁም የባለ ሁለት ጎማ ሞተር አደረጃጀት መመሪያ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል::

ጥር 17 /2016 ዓ.ም

newz31

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የመንገድ ልማት ሥራዎች ያለበትን ደረጃ ገመገሙ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የመንገድ ልማት ሥራዎች ያለበትን ደረጃ ገመገሙ::

ግምገማ የተደረገው የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ በበጀት ዓመቱ በመንገዶች ባለስልጣን በኩል እና በገጠር ተደራሽ መንገድ በዩራፕ ዘርፍ ታቅዶ እየተገነቡ ያሉትንና የጥገና መንገዶች እንዲሁም የድልድይ ግንባታ ሥራዎች የግምገማዉ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እየተገመገመ ይገኛል::

በመድረኩም የርዕሰ መስተዳድር አማካሪዎች የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እና የማናጅመንት አባላት የአራቱም ዞን የፊት አመራሮች እንዲሁም የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የፅ/ቤት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል::

በግምገማዉም መድረክ ላይ በመንገዶች ባለስልጣንና በዩራፕ ዘርፍ የታቀዱና በ6 ወር ዉስጥ እስከ አሁን ያለው አፈፃፀምን በተመለከተ የተዘጋጀ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል::

በቀረበው የሪፖርት ሠነድ መነሻ የመድረኩ ተሳታፊዎች ከእቅድ አፈፃፀም አንፃር ያለውን ሁኔታ ከዞን እና ወረዳዎች ደረጃ እታች ያለውን ጉድለትና ጥንካሬ አንስቷው በቀጣይ ልስተካከሉ የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮችን በአራት ቡድን ተከፍሎ ጥልቀት ያለው ውይይት እየተደረገ ነው::

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቀጣይ ትኩረት የሚደረጉ በተለይ የዝናብ ወቅት ሳይገባ ቶሎ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅና ከመንገዶች ጥራት አንፃር በቢሮ ደረጃ ትኩረት ልሰጡ የሚገቡ ጉዳዮች ተለይቶ ውይይት በማደረግ ልፈቱ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የውይይት አቅጣጫ ተደርጓል::

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የተጀማመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑ አንስተዉ በቀጣይ ከጊዜ ጋር ተያይዞ የምታዩ ችግሮች መፈታት የሚገባቸውና ከመንገዶች ጥራትና እስታንዳርድ ረገድ የሚታዩ ጉድለቶች በተለያ ከግብአት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተስተዋሉት በፍጥነት መታረም ያለባቸው እንደሆነ አቅጣጫ ተቀምጦ ለመንገዶች ግንባታ ስራዎች ሁሉም አካላት መቀናጀት እንዳለባቸዉ ገልፆዎ የቡድን ውይይቱ በጥልቀት በዞን ማዕከል አመራር እየተመራ እየተደረገ ይገኛል::

ከቡድን ውይይት በመቀጠል በጋራ ቡድን ሪፖርት ቀርቦ ማጠቃለያ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል::

ጥር 9 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

newz82

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልል ደረጃ እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልል ደረጃ እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ::

ርዕሰ መስተዳድሩ ጉብኝት ያደረጉት በክልሉ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ፣ በመንገዶች ባለስልጣን እና በቢሮው ዩራፕ ዘርፍ የተሰሩ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን ነው::

በጉብኝቱም የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ምክትል ፕሬዘደንት ክቡር አቶ በየነ ባራሳ፣ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አመራሮች፣ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እና የማናጅመንት አባላት ተገኝተው እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል::

በበጀት ዓመቱ በዩራፕ ዘርፍ የግንባታ ፕሮጀክቶች 26 የመንገድ ፕሮጀክቶች 153.5 ኪሜ እንዲሁም የጥገና ፕሮጀክቶች 28 መንገድ 198 ኪሜ በክልሉ መንግስት በጀት ተይዞላቸው እየተገነቡ የሚገኙ መንገዶች ተጎብኝቷል::

በበጀት ዓመቱ ሁሉም ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እቅድ ተይዞ እየተሰሩ እንደሆነ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በመስክ ምልከታ ወቅት ገልጸዋል::

በጉብኝቱም ወቅት የመንገድ ስራዎች በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች ጥራታቸዉ ተጠብቆ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ሁሉም አካላት መረባረብ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ገልጸዋል::

ጥር 7 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

newz45

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እና የማናጅመንት አባላት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ያሉበትን ደረጃ ጉበኝት አደረጉ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እና የማናጅመንት አባላት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ያሉበትን ደረጃ ጉበኝት አደረጉ::

የመስክ ጉበኝቱ ከቦርጃ ውጅግራ ፕሮጀክት የ5.56 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን የፕሮጀክት ስራዎች ያሉበትን ለማየት ተችሏል:: የመንገዱ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለማየት ችለናል::

የመንገዱ መገንባት የማልጋ እና የወንዶ ገነት ወረዳን የሚያገናኝ በመሆኑ ለአከባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እጅግ በጣም ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መንገድ እንደሆነ በምልከታ ወቅት ለማረጋገጥ ችለናል:: ለዚህም ፕሮጀክት ሁሉም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዞን እና ወረዳ አመራሮች በቅርበት ክትትል ማድረግ የሚገባው እንደሆነ ተገልፆዋል::

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ዉስጥ እስከ ጥር 30/2016 ዓ. ም ድረስ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ የእስታር የሥራ ተቋራጩ አስተባባሪዎች አሳውቋል:: ፕሮጀክቱ በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቅ የቢሮ ማናጅመንት አመራሩ በቅርበት ክትትል እንደሚያደርጉ ገልፃዋል::

ጥር 3 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

newz22

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ::

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ::

በመድረኩ የቢሮ ኃላፊ ክቡር ታምሩ ታፌ የቢሮ ማናጅመንት አባላት እንዲሁም አጠቃላይ የቢሮ ባለሙያዎች ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆኗል:: በግምገማ መድረኩም የ6 ወር የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሠነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል::

በቀረበው ሪፖርት መነሻ በ6 ወር ዉስጥ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ዘርፎች እና ዳይረክቶሮቶች በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ እና በአፈፃፀማቸው በመካከለኛ ደረጃ ያሉና ወደ ኃላ የቀሩ ዘርፎች እና ዳይረክቶሬቶች በቀጣይ ቀሪ ወራት በጉድለት የተለዩ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥተው እንዲከናወኑ አቅጣጫ ተቀምጧል::

በመጨረሻም በቢሮ ደረጃ የሚከናወኑ ቁልፍ ቁልፍ ተግባራት በሙሉ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ዉስጥ በውጤታማነት እንዲከናወኑ ተግባቦት ላይ ተደርሶ የግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ተደርጓል::

 ታህሳስ 26 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ