newu1

በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::

በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::

በምክክር መድረኩ በዞን ደረጃ እየተሰሩ የሚገኘው የግንባታ እና ጥገና መንገዶች እንዲሁም የድልድይና እስትራክቸር ስራዎች አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ተገምግሟል::

ኮንትራክተሮቹ ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች ከተቀረፈላቸው ፕሮጀክቶቹን በተባለው ጊዜ ዉስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል::

የፕሮጀክቶች አፈፃፀም በጥራት አጠናቆ ከማስረከብ አንፃር የሚታዩ ችግሮች ; የኮንትራክተሮች የአፈፃፀም ፍጥነት ጊዜን ታሳቢ በማድረግ ከመስራት ረገድ የሚታዩ ችግሮች በቀጣይ ልታረሙ የሚገቡ እንደሆኑ ተገምግሟል::

የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ኖኦራ በመድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት :- በዞን ደረጃ በቢሮ በኩል መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ እንዲሰራ እያደረገ በመሆኑ ከአቅርቦት ጋር የሚታዩ ችግሮችን ለመንገድ እና ድልድይ መሰረተ ልማት ቅድሚያ እንዲሰጥ ለማድረግ ርብርብ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል::

በቢሮ በኩል የተጀመረው የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በማድረግ ፕሮጀቶች በጥራት እንዲሰሩ ማድረግ የሚገባዉ እንደሆነ የቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል ::

ኮንትራክተሮች ዉል በገቡት መነሻ በማጠናቀቅ ለአከባቢ ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንፃር ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው የቢሮ ኃላፊ ጨምሮ ተናግረዋል::

በመጨረሻም በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቢሮ ኃላፊ በዞኑ የተያዙ እና እየተሰሩ ያሉትን ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ መልኩ በማከናወን ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ በማድረግ ሕብረተሰብን  ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::

በመጨረሻም በቢሮ በኩል ጠንካራ የክትትል እና ግምገማ ስርዓት የተዘረጋ በመሆኑ በፕሮጀክት ሳይት ደረጃ የሚታዩ ችግሮች እየተፈቱ እንዲሄዱ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል:

በግምገማ መድረኩ የቢሮ  ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ; የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ኖኦራ ; የተጠሪ ተቋም አመራርና ባለሙያዎች; የምስራቃዊ ሲዳማ  ዞን  የመምሪያ አመራሮች እንዲሁም ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች ተገኝተዋል::

   =======================

የካቲት, 19/2018 ዓ.ም

በንሳ, ዳዬ

neww12

የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::

የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::

በሲዳማ ክልል የመናኸሪያዎች አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ በመደረጉ አገልግሎቱን ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራዉ የጉብኝት ቡድን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ እና በአሮጌ መናኃሪያዎች ተገኝተዉ የአገልግሎት አሰጣጡን ሂደት ምልክታ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጡ ሂደት የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ቢሮዉ በክልሉ የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርትን መመሪያ በማዘጋጀት ተግባራዊ እያደረገ በመሆኑ በትራንስፖርት በኩል የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ በምልክታ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

በወጣቶች የተደራጁ ማህበራት ሁሉም የቢሮ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እጣ በማንሳት ከቢሮው ጋር ዉል ገብተው ወደ ስራ ከገቡ ወዲህ ያለው የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የተቀመጡ ተግባራትን መነሻ በማድረግ እየተሰሩ ያሉበትን ሁኔታ የቢሮ ማናጅመንት አመራሮች ጎብኝተዋል፡፡

በሁለቱም  መናኃሪያዎች ዉስጥ የተገልጋይ ማረፊያዎች፤የመጸዳጃ ቦታዎች እንዲሁም ለተገለጋይ ትኬት የሚሰጥበት አከባቢ ይበልጥ እንዲለማ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባቸው ተብራርቷል፡፡

የተሸከርካሪዎች መግቢያ እና መዉጫ፤የዲጂታል ሚዛን፤ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዲስፕለይ ማድረጊያ እስክሪኖች እንዲሁም በካሜራ የታገዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት የተደራጁ ማህበራት ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሆነ መመልከት ተችለዋል፡፡

በሌላም በኩል ከትራፊክ ፖሊሰ እና ከመናኃሪዎች አስተባባሪዎች ጋር በቅንጅት በመስራት አገልግሎቱን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿዋል፡፡

የተደራጁ ወጣቶች የሲና ሀርድ እንዲሁም የስታር ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ማህበራት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም የእዉቀት ሸግግር በማድረግ ወጣቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርትን ተግባራዊ ለማደረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች ዉጤቶች እየታበት በመሆኑ በቀጣይም በመመሪያዉ ዉስጥ የተካተቱ አገልግሎቶች በሙሉ እንዲጀመሩ በቅርበት ድጋፍ ክትትል እንደሚደረግ የቢሮ ሃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ የቢሮ አመራሮች፤የሀዋሳ ከተማ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

        =====================

የመንግስት ኮሙኒኬሸን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ጥር/2018 ዓ.ም

ሀዋሳ፥ሲዳማ

newz1986

የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::

የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::

ሴክተሩ በገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና (RCFSP) ፕሮግራም አማካይነት የተለገሱ 7 ያማሀ ሞተር ሳይክሎችን በፕሮጀክቱ ለሚደገፋ 7 ወረዳዎች የርክክብ መርሀ- ግብር አከናውኗል:: የቢሮ ሀላፊው አቶ ጎሳዬ  ጎዳና ለወረዳ ፅ/ቤት ሀላፊዎች የቁልፍ ርክክብ ሥነ- ሥርዓት ሲያደርጉ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል::

ይህ በፕሮጀክቱ አማካይነት ከፌዴራል መንግስት ያገኘናቸው 2 ሀርድ ቶፕ መኪናዎች፣ 7 ሞተር ሳይክሎች የ100 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀምን ግብረ- መልስ እየሰጠን ባለንበት ወቅት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል::

የፕሮጀክቱ ድጋፍ የመንገድ ልማት ተግባራችንን የበለጠ ቀልጣፋና የተሳለጠ ያደርገዋል ሲሉ አብራርተዋል::

በመሆኑም እነዚህ የተለገሱ ተሽከርካሪዎች በወረዳዎች የሚሰሩትን መንገዶች በቅርበት ለመደገፍና ለመከታተል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ::

ከዚህ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ ጠንክራችሁ ከሰራችሁ ለመንገድ ሥራ የሚውሉ ማሽነሪዎችን እንደሚሰጡን ቃል መግባታቸውን አስረድተዋል::

የወረዳ ፅ/ቤት ሀላፊዎችም ኮንትራክተሮች የመንገድ ሥራውን ሲያከናውኑ ለሚገጥማቸው እንደ ነዳጅ ያሉ የዕጥረት ተግዳሮቶችን ከሚመለከታቸው የዞን አመራር ጋር በመቀናጀት መፍትሄ በማበጀት ልትደግፉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል::

በመጨረሻም እነዚህን ሞተር ሳይክሎች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ በማዋል ልማቱን በማሳለጥና በአግባቡ በመጠቀም ልትገለገሉ ይገባል ሲሉ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል::

 ታህሳስ – 27/ 2018 ዓ.ም

 ሀዋሳ

newx11

በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::

በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::

በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ እና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞኖች በቢሮ በኩል ግንባታቸው እየተከናውኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን  በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና በተመራው ቡድን ምልከታ ተደርጓል::

በሪካፕ ፕሮግራም በኩል የጥገና ሥራ ተጠቃሎ ሪክክብ የተደረገዉ በጎርቼ ወረድ የሚገኘ የዊጣ ጎርቼ ፕሮጀክት በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለማየት ተችሏል::

በመንገዶች ባለስልጣን በኩል እየተገነባ የሚገኘው የዎላ ጃልዶ ቡሳዋ የ14 ኪሜ ማቴሪያል የመበተን ሥራ በጥሩ ሁኔታ ጥራቱ ተጠብቆ እየተሰራ ይገኛል::

መንገዱ የጎርቼ ሻፋሞ እና የአርቤጎና ወረዳዎችን የሚያገናኝ በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥተው እየተገነባ ይገኛል::

በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በዎንሾ ወረዳ የጥገና ስራው እየተሰራ የሚገኘው የቦካሶ ዳዋሌ መንገድ ጠጠር የማልበሱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ምልከታ ተደርጓል::

ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በወንዶ ገነት ወረዳ በዩዎ አከባቢ አዲስ እየተከፈተ የሚገኘውን መንገድ የከፈተ እና የአፈር ሥራ እየተሰራ  ያለውን እንቅስቃሴ በምልከታ ወቅት ለማየት ተችሏል::

የመስክ ምልከታ እና የድጋፍና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ታህሳስ 01/04/2018 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

newy7

በሲዳማ ክልል የዩራፕ ፕሮጀክቶች ዋጋ ማሻሻያ ጥናት ላይ ምክክር ተደረገ::

በሲዳማ ክልል የዩራፕ ፕሮጀክቶች ዋጋ ማሻሻያ ጥናት ላይ ምክክር ተደረገ::

በሲዳማ ክልል በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸው በሚከናወኑ የመንገድ እና የድልድይ ግንባታዎች የዋጋ ማሻሻያ ጥናት ቀርቦ ምክክር ተደረገ ::

በምክክር መድረኩ በጥናት ቡዱኑ ኮሚቴ አባላት በክልል ደረጃ ዋጋ ማሻሻያ ለማድረግ መሰረታዊ ምክንያት የሆኑ ጉድዮች ተለይቶ ጥናት እንደተደረገ ከቀረበዉ የጥናት ሠነድ ለማረጋገጥ ተችሏል::

በመድረኩ ተገኝተው የጥናቱን አስፈላጊነት በክልል ደረጃ ከክልሉ መንግስት ምክር ቤት አባላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አባላት በተገኙበት ምክክር በማድረግ ፀድቆ በሥራ ላይ እንዲዉል ለማድረግ እንደሆነ የርዕሰ መስተዳደሩ ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ ተናግረዋል::

በክልል ደረጃ በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸዉ የሚከናውኑ ድልድዮች፥ የመንገድ ጥገና እና ግንባታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ በየጊዜው የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ጥራት ያለው ሥራ እንዲሰራ ለማድረግ እንደሆነ ከቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና በኩል ተገልጿል::

የዋጋ ማሻሻያን በተመለከት በሀገር ደረጃ የግንባታ እቃዎች ዋጋ መጨመር፣ የጥገና ዋጋ መጨመር፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፣ እንዲሁም የሠራተኞች ክፍያ እንደ ምክንያት የተለዩ ጉዳዮች እንደሆነ ከቀረበው የጥናት ሠነድ ተመላክቷል::

በቢሮ በኩል የተደራጀዉ የጥናት ቡድን ከ ሲዳማ ክልል የኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኩል ተገምግሞ የዳበረ ሲሆን በቀረበዉ መነሻ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ተጨማሪ መደረግ የሚገባቸዉ ጉዳዮች ተለይቶ እንዲቀርብ በመድረኩ የተገኙት የካቢኔ አባላት ተናግረዋል::

የሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ የሚጀመሩ ፕሮጀክቶች በጥራት እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባ ከመድረኩ ተገልጿል::

የጥናቱ ሥራ በተያዘለት ጊዜ ዉስጥ እንዲጠናቀቅ የመንገድ ልማትና ትራስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት ወቅታዊ የዋጋ ሁኔታን መነሻ በማድረግ ጥናቱን አጠናቆ እንዲያቀርቡ እና ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል::

በመድረኩ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ፣ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና፣  የካቢኔ አባላት፣ የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች፣ የኮንስትራክሽ ባለስልጣን ኃላፊ እንዲሁም ጥናት ቡዱን አባላት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ህዳር 17/2018 ዓ.ም.

newx45

የአከባቢና ማህበራዊ ክዋኔ ኦዲት በተቀናጀ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ተገለፀ::

የአከባቢና ማህበራዊ ክዋኔ ኦዲት በተቀናጀ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ተገለፀ::

በሲዳማ ክልል በRCFSP ፕሮግራም   አተገባበር ዙሪያ በሲዳማ ክልል የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በኩል የ2017 በጀት ዓመት የአከባቢ እና ማህበራዊ ጉዳዮች አጠባበቅ ዙሪያ የተከናውኑ ተግባራት የክዋኔ ኦዲት ግምገም ሪፖርት የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና በተገኙበት ተገምግሟል::

ፕሮግራሙ በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ  በመሆኑ ሁሉም  ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው በመድረኩ ተገልጿል::

በግምገማው በቀረበዉ የክዋኔ ኦዲት የመንገዶች እና ስየአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን መንገዶችን ስፔሻል እስትራክቼሮች በአጠቃላይ ወደ 66% የሚሆኑትን በመለየት ኦዲት እንደተደረገ ከሪፖርቱ ለመመልከት ተችሏል::

በፕሮግራሙ የአከባቢ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን ላይ ትኩረት በማድረግ በአንዳንድ አከባቢዎች በማህበረሰቡ ላይ ተፅእኖ የምፈጥሩ ጉዳዮች ተለይቶ በቀጣይም ኦዲቱን መነሻ ተደርጎ ጠንካራ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተብራርቷል::

የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን ጋር በቅርበት በመስራትየሚታዩ ችግሮችን እየለዩ ማረም የሚገባዉ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽታዬ ዩሙራ ተናግረዋል::

የመንገድ ጥራትን እና ስታንዳርድ በዓለም ባንክ የወጣዉን መነሻ በማድረግ በአከባቢ እና ማህበረሰብ ደረጃ ጉዳት እንዳያደርሱ መስራት እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል::

በክልል ደረጃ ተገባራዊ እየተደረገ የሚገኘዉ ፕሮግራም ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በቢሮ በኩል እንዲሁም በፕሮግራም ሰራተኞችና በባለድርሻ አካላት በኩል ጠንካራ ቅንጅት ተፈጥሮ እየተሰራ መሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ተብሏል::

በክልል ደረጃ የማተሪያል ማምረቻ ቦታዎች መልሶ በማልማት ለሌላ አደጋ እንዳይዳረግ ፕሮጀክቶችን እየሰሩ የሚገኙ ኮንትራክተሮች መልሶ በማልማት ማህበረሰቡን ከአደጋ እንዲሁም አከባቢውን ከጉዳት መከልከል ላይ ትኩረት እንዲደረግ በሰነዱ ተብራርቷል::

የቢሮ ኃላፊ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ፕሮግራሙ በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተደረገ የሚገኝ በመሆኑ ጥራት ያለውን ሥራ በመስራት በሰባቱም ወረዳዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል::

በመጨረሻም በክልሉ የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በክዋኔ ኦዲት በኩል የተለዩ ጉድለቶችን ጊዜ ሳይሰጥ ማረም እንደሚገባ ገልጸዋል::

በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት በጋራ  ተግባሩን እየገመገሙ ጠንካራ የኦዲት ሥራዎች እየተሰሩ ህዝባችን በፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይበልጥ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ ባለመሆኑ ቅንጅቱን ማጠናከር እንዲሁም በቀሪ ወረዳዎች  ፕሮጀክቶች ባሉበት  ትኩረት በመስጠት ከአመራራና ከኮንትራክተሮች ጋር በቅርበት ቼክ ሊስትን በማዘጋጀት መስራት እንደሚያስፈልግ የቢሮ ኃላፊ አቅጣጫ አስቀምጧል::

በመድረኩ የቢሮ አመራሮች;የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን  ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽታዬ ዩሙራ; የፕሮግራሙ ሠራተኞች እና በኦዲት ሥራ ላይ የተሳተፉ ሠራተኞች ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል::

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ህዳር 08, 2018 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

newx1

ከፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር ምክክር ተደረገ::

ከፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር ምክክር ተደረገ::

በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው  የRCFSP ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ በክልሉ በፕሮግራሙ የታቀፉ የባለድርሻ አካላት በሙሉ በተገኙበት ከድጋፍ እና ክትትል ቡድን ጋር  ውይይት ተደርጓል ::

የድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ የነበሩ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች ተለይቶ እንዲሁም የ2018 በጀት በሚሰሩ ፕሮጀክቶች አንፃር ትኩረት በማድረግ ሠነድ በድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ ቀርቧል::

በመድረኩ የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት ፕሮግራሙ በክልላችን በ7 የተመረጡ ወረዳዎች ተግባራዊ እየሆነ ያለ በመሆኑ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በማከናወን ዉጤታማ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል ::

ከፌደራል የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች በክልሉ ያለው የ2017 በጀት ዓመት የተሻለ ዉጤት የመጣበት ክልል በመሆን ሁለተኛ ወጥቶ እዉቅና ያገኘ ክልል እንደመሆኑ በ 2018 በጀት ዓመት የተያዙ ፕሮጀክቶችን በሙሉ ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ለማድረግ በጊዜ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል::

በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ ፕሮግራም እንደመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት የሚጠበቅ መሆኑ ተገልፆ አማካሪዎች እና ኮንትራክተሮች  አቅማቸውን ሙሉ እንዲጠቀሙ ከማድረግ አንፃር ጠንካራ ቁጥጥር ከማድረግ ረገድ የሚታዩ ችግሮች በዚህ በጀት ዓመት ልታረሙ እንደሚገባ ተገልጿል::

በመድረኩ የተገኙት የባለድርሻ አካላት ይሄ ፕሮግራም በክልሉ የታቀፉ ወረዳዎች የመንገድ ግንባታና ጥገና እንዲሁም የድልድይ ግንባታዎች ማህበረሰብን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ አስፈላጊ ድጋፍ  እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::

የቢሮ ኃላፊ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ከዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ ፕሮግራም በመሆኑ የፌደራል የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በቅርበት ድጋፍ እና ክትትል እንዲያደርጉ እና በክልል ደረጃ የተደራጀዉ የስትሪንግ እና የቴክኒክ ኮሚቴ በየጊዜው እየተገመገመ እንደሚመራ ተናግረዋል::

በመጨረሻም ባለፈው ዓመት ተግባራዊ ሲደረጉ የነበሩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በቢሮ በኩል ጠንካራ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የሚመጣውን በጀት እና ድጋፍ ለታለመለት አላማ ለማዋል በ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል::

በድጋፋዊ ክትትልና  ምክክር መድረክ ላይ የቢሮ አመራሮች ፣ የፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የድጋፍ ቡድን ፣ የግዥ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፣ የአከባቢ እና አየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን ኃላፊ ፣ የክልሉ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፣እንዲሁም የሪካፕ ፕሮግራም አስተባባሪ ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል::

ህዳር 02/2018 ዓ.ም 

ሐዋሳ, ሲዳማ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

newz 234

ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳና የዘመነ የአመራርና ባለሙያዎች ትጋት ለተቋም ግንባታ ቁልፍ እንደሆነ ተገለፀ::

ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳና የዘመነ የአመራርና ባለሙያዎች ትጋት ለተቋም ግንባታ ቁልፍ እንደሆነ ተገለፀ::

ለሴክተሩ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች  የአቅም ግንባታ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደዋል።

 ቢሮ ሀላፊው ሲናገሩ :- የቢሯችን አመራርና ባለሙያዎች ከብልሹ አሠራርና የሠራተኞችን አዋጅ ደንብና መመሪያን በአግባቡ ከመተግበር አንፃር ምን እንደምንመስል ራሳችንን ለመመልከት ይረዳን ዘንድ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል።

አክለውም አቶ ጎሳዬ ይህ መድረክ ሁላችንም ብልሹ አሠራርን እንድንጠየፍና የሠራተኞች አዳዲስ የወጡ አዋጆች: ደንቦችና መመሪያዎች ያለንን ግንዛቤ በማሳድግና ግልፀኝነት በመፍጠር ድርሻው የጎላ እንደሚሆን እምነቴ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በተቋሙ ሊከሠቱ የሚችሉ ብልሹና ተገቢ ያልሆኑ አሠራሮችን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለማቀጨጭ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ ይደረጋል ሲሉ አስገንዝበዋል ።

በመድረኩ ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በአዳዲስ አዋጆች ላይ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሠራርን አስመልከቶ ደግሞ ከፀረ- ሙስና ኮሚሽን በተጋበዙ አሠልጣኞች የሥልጠና ሠነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ከተሣታፊዎችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ከመድረክ ምላሽ ተሠጥባቸዋል።

 

በመጨረሻም ከመድረኩ በቀጣይ ለሚኖሩን ተግባራት በአመራሩና  ባለሙያዎች መካከል ጠንካራ ቲም እስፕሪት በመፍጠርና ግልፀኝነት በማጎልበት በዕቅድ በመመራት ውጤታማ ሥራ ለመሥራት  ከስምምነት በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል ።

ጠንካራ የአመራር ሥርዓትና የባለሙያዎች ትጋት የተቋምን ገፅታ ይቀይራል!!

ጥቅምት 2018 ዓ.ም

ሀዋሳ