በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::
በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ እና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞኖች በቢሮ በኩል ግንባታቸው እየተከናውኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና በተመራው ቡድን ምልከታ ተደርጓል::
በሪካፕ ፕሮግራም በኩል የጥገና ሥራ ተጠቃሎ ሪክክብ የተደረገዉ በጎርቼ ወረድ የሚገኘ የዊጣ ጎርቼ ፕሮጀክት በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለማየት ተችሏል::
በመንገዶች ባለስልጣን በኩል እየተገነባ የሚገኘው የዎላ ጃልዶ ቡሳዋ የ14 ኪሜ ማቴሪያል የመበተን ሥራ በጥሩ ሁኔታ ጥራቱ ተጠብቆ እየተሰራ ይገኛል::
መንገዱ የጎርቼ ሻፋሞ እና የአርቤጎና ወረዳዎችን የሚያገናኝ በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥተው እየተገነባ ይገኛል::
በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በዎንሾ ወረዳ የጥገና ስራው እየተሰራ የሚገኘው የቦካሶ ዳዋሌ መንገድ ጠጠር የማልበሱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ምልከታ ተደርጓል::
ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በወንዶ ገነት ወረዳ በዩዎ አከባቢ አዲስ እየተከፈተ የሚገኘውን መንገድ የከፈተ እና የአፈር ሥራ እየተሰራ ያለውን እንቅስቃሴ በምልከታ ወቅት ለማየት ተችሏል::
የመስክ ምልከታ እና የድጋፍና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 01/04/2018 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::