new new 129

ለተቋማት የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል።

ለተቋማት የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል።

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ከሴክተሩ አመራርና ባለሙያዎች ትውውቅ ጋር አድርገዋል።

በትውውቅ መድረኩ  የቢሮ ሀላፊው  በመልዕክታቸው:- በቀጣይ የሚኖረን የስራ ዘመን ለተቋሙ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራትን ቀልጣፋ እናደርጋለን፣ ቀደም ሲል የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በማጎልበት ባሉት ጉድለቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ርብርብ ይደረጋል፣ የምንሠራው ሥራ ብዙሀንን ማከለ መሆን አለበት ብለዋል።

አክለውም የተቋሙ ሠራተኞች ምቹ ውጤታማ ማድረግና ሠላማዊ የሆነ የሥራ ግንኙነት መፍጠር ይገባል። እንዲሁም ለባለሙያው የሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎእንዲሰጡና ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲዘምን አስፈላጊው ጥረት ሁሉ ይደረጋል በማለት አመላክተዋል።

ከዞንና ወረዳዎች ጋር የሚኖረው ዲፕላማሲያዊ ግንኙነትና ትስስር የበለጠ እንደሚጠናከር ተገልጷል።

በመድረኩም የእንኳን ደህና መጣህ የኬክ ቆረሳ መርሀ – ግብር ተከናውኗል ።

በልማት ልቅድ ዳይሬክተር አማካኝነት የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም እቅድዋና ዋና አቅጣጫዎች ሠነድ በመድረኩ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል ።

ከተሣታፊዎች ያለፋትን ጉድለቶች የሚያርሙና በቀጣይ ጠንክሮ ከሀላፊው ጋር አብሮ ለመስራት የሚያችሉ አስተያየቶች ተሠጥተዋል።

በፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ፍጥነት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ጠንካራ ቅንጅዊ አሰራርን በመዘርጋት በክልሉ በመንገድ እና ድልድይ ግንባታዎች በኩል የሚታዩ ችግሮች ትኩረት ተሰጥተው እንደሚሰራ ገልፆል::

በመጨረሻው ሀላፊው መድረኩን ሲያጠቃልሉ:- የተነሱትን ሀሳቦች በመገንዘብ በቀጣይ የሚኖረን የሥራ ዘመን መልካም የሥራ ግንኙነት ፈጥረን የተቋሙን ገፅታ በመቀየር አገልግሎነት አሠጣጡን ለማሳደግ የሚቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል።

መልካም የስኬት ፍሬ የምናፈራበት የብልፅግንና ዘመን እንሆንልን እመኛለሁ በማለት መድረኩ ተጠናቋል።

መስከረም 28 / 2018 ዓ.ም

 ሀዋሳ

የዘገበው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው!

newhn

በመናኸሪያዎች እየተተገበረ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ (E-ticket) አገልግሎት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ተገለፀ።

በመናኸሪያዎች እየተተገበረ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ (E-ticket) አገልግሎት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ተገለፀ።

በሲዳማ ክልል በሚገኙ መናኸሪያዎች እየተሰጠ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ቀደም ሲል ምንም አይነት ህግ፣ ደንብና መመሪያ ያልተዘጋጀለት  እንደሆነ የገለፁት የቢሮ  ሀላፊው አቶ ጎሳዬ ጎዳና ናቸው።

የቢሮ ሀላፊው እንዳሉት የትራንስፖርት አገልግሎቱን በማቀላጠፍ፣ ተሣፋሪውን ከህገ ወጥ ክፍያ በማዳንና ከወንበር በላይ ባለ መጫን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት እስካሁን የህግ ማዕቀፍ ሳይበጅለት መቆየቱን በቁጭት ተናግረዋል።

ስለሆነም አሁን እየተዘጋጀ ያለው ህግ፣ ደንብና መመሪያ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩትን ተግዳራቶችንና የመናኸሪያዎችን መሠረተ- ልማት በማበልፀግ የሚጫወተው ሚና የጎላ እንደሚሆን በአፅንኦት አስረድተዋል ።

አክለውም ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢ- ቲኬቴንግ አገልግሎት በለሙት ሶፍትዌሮች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችም ተወዳዳሪ በመሆን የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል።

የዚህ ደንብና መመሪያ ዝግጅት ተደራጅተው የሚቀርቡትን ማህበራት ለማወዳደርና አሸናፊውን በትክክል ለመለየት ያስችላል።

የመናኸሪያዎችን ገፅታና መሠረተ ልማት በማሳደግ  የውስጥ ገቢያቸው እንዲጨምር የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል።

በውይይቱ እየተዘጋጀ ባለው ደንብና መመሪያ ላይ ገንቢ አስተያየታቸውን ያካፈሉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ እንዲሁም የቢሮው ማናጅመንት አካላት ናቸው።

ከመድረኩም መመሪያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ በሀዋሳ ከተማ በዞኖችና ወረዳ ከተማዎች በሚገኙ መናኸሪያዎች  ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሟል ።

መስከረም 27/2018 ዓ.ም

ሀዋሳ

newz 12345

በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የRCFSP ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ::

በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የRCFSP ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ::

በRCFSP ፕሮግራም ለታቀፉ ወረዳዎች በፕሮግራሙ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ, በ2017 አፈፃፀም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ ላይ የምክክር መድረክ ከወረዳ አመራርና  ፎካሎች ጋር ስብሰባ (Review meeting) ተደርጓል::

ከእቅድ ዝግጅት ግምገማ በፕሮጀክቱ በታቀፉት ወረዳዎች  እየተሰሩ ያሉትን ፕሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ዉስጥ  እንዲጠናቀቁ ለማድረግ  ከፕሮጀክት አማካሪዎች እና ኮንትራክተሮች ጋርም ምክክር መደረጉ ተገልጿል::

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቢሮ ኃላፊ እንደገለፁት በወረዳዎች ተገባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የመንገድ እና ድልድይ ስራዎችን በቅርበት በወጣው እስታንዳርድ መነሻ ክትትል በማድረግ ሚናቸዉን እንዲወጡ ተናግረዋል::

በሌላም በኩል ሁሉንም ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ጥገናን በተመለከተ ከአማካሪዎች ጋር በመሆን ቁጥጥር በማድረግ የተያዘው በጀት ለተባለለት አላማ እንዲዉ ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ ጨምሮ ገልጿል::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር ታምሩ ታፌ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች እና የሰባቱም ወረዳ አመራሮች ; አማካሪዎች እንዲሁም የወረዳ ፎካል ባለሙያዎች ተገኝተው ተሳተፉ ሆነዋል::

መስከረም 10/2018 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

11111

የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ::

የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ::

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በክልል ደረጃ እየደረሰ ያለዉን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሂዷል::

የምክክር እና ስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የመንገድ ደህንነና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኮሮነል ሮዳሞ ኪአ እንደተናገሩት በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተናግሯል::

በሲዳማ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት ከ 2014 እስከ 2017 ድረስ ብቻ 474 ዜጎች በሞትእና 313 ዘጎች ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን እና ከ 30 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ንብረት መዉደሙን ገልፆዋል::

በሌላም በኩል በ 2017 በጀት ዓመት ብቻ ወደ 180 ዜጎች በመንገድ ትራፊክ አደጋ የሞት አደጋ የደረሰባቸው እንደሆነ አስረድቷል::

በተጨማሪም በክልል ደረጃ 89.9 % አደጋ እየደረሰ ያለዉ ከተፈቀደው ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከሩ መንስኤ መሆኑን ጠቅሰዉ አስከርካሪዎች ለዚህ ሚናቸው ከፍተኝበመሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል::

የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት በብቃት በማሰልጠን  ኃላፊነታቸዉን በመዎጣት መንግስት ያወጣዉን ደንብ እና አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ እንዲወጡ አሳስቧል::

በክልል ደረጃ ለትራፊክ አደጋ መከሰት መንስኤ ከሆኑት ጉዳዮች ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት, አሽከርካሪዎች  ደንብን አለማሽከርከር ለትራፊክ  አደጋ መከሰት ምክንያት መሆኑን ገልፆዋል::

በሌላም በኩል የተሽከራካሪ ብቃት ማረጋገጫ ተቋማት በቃት ሌላቸው ተሽከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት የሚታዩ ችግሮች መሆኑ ተነስቷል::

በምክክሩ መድረክ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት የሚደርሱ የመንገድ ትራፊክ አደጋን የመከላከል ጉዳይ ለመንግስት አካላት ብቻ የሚተዉ ሳይሆን የማሰልጠኛ ተቋማት, የትራንስፖርት ማህበራት የቴክኒክ ምርመራ እንዲሁም ኢንሹራንሶች አደጋዉን ለመቀነስ ሚናችን ትልቅ በመሆኑ ግዴታቸንን እንወጣለን በማለት ገልፆዋል::

በመጨረሻም የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኮሮነል ሮዳሞ ኪአ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሬ ሪቂዋ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል::

በምክክር መድረኩ ላይ የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች የክልል ፖሊስ ኮሚሽን, የሐዋሳ ከተማ የመ/ል/ት/መምሪያ ኃላፊዎች የ ትራንስፖርት ማህበራት,የማሰልጠኛ ተቋማት, እንሱራንሶች እንዲሁም የባለድርሻ አካላት በሙሉ ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል::

ነሐሴ, 2017 ዓ.ም ሐዋሳ

newz100012

በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የህብረተሰብ ተሳትፎ ሥራ ድጋፍ እና ክትትል ግብረ መልስ ተሰጠ፡፡

በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የህብረተሰብ ተሳትፎ ሥራ ድጋፍ እና ክትትል ግብረ መልስ ተሰጠ፡፡

በበጀት ዓመቱ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የመንገድ እና ድልድይ ግንባታ መሰረተ ልማትን ለማፋጠን ትኩረት ተሰጥተዉ እየተሰራ የቆየ ሲሆን በመንግስት በጀት ብቻ በየዓመቱ በጀት ተይዞ የማህበረሰቡን የመንገድ ጥያቄዎችን መመለስ አስቸጋር በመሆኑ ህበረተሰቡን በማሳተፍ የመንገድ እና የድልድይ ግንባታ ሥራዎች በሁሉም ወረዳዎች እንዲከናወኑ ተደርጓል፡፡

በዚህም በዓመቱ ለማከናወን ዕቅድ ከተያዙ አዳዲስ የመንገድ ከፈታ እና የጥገና ስራዎች እንዲሁም የድልድይ ግንባታ ከመንግስት በጀት ዉጪ ህበረተሰቡን በማሳተፍ በርካታ ተግባራትን ማከናወን እንደተቻለ ለዞኖች በዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎችን መነሻ በማድረግ ግበረ መልስ በተሰጠበት ወቅት ተገልጿል፡፡

በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ደረጃ ህበረተሰቡን በማሳተፍ በተሰራው ስራ በሁሉም  ወረዳዎች አደረጃጀቶችን እስከ ቀበሌ ድረስ በመጠቀም በሁሉም ቀበሌያት በልማት ቡድን ንቅናቄ ተደርጎ በተሰራዉ ሥራ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ መሆን መቻሉን በተሰጠው ግብረ መልስ በተሰጠበት ወቅት ተገልጿል:: 

በዞን ደረጃ ከቢሮ ጋር በመቀናጀት እስከታችኛዉ መዋቅር ድረስ እቅድ በማዉረድ እንዲተገበር ለማድረግ በተቀመጠዉ እስታንዳርድ መሰረት ከ6-8 ሜትር  ድረስ እንዲሰራ መግባባት ላይ ተደርሶ የከፈታ እና ጥገና ሥራ ማከናወን መቻሉን  ተገልጿል፡፡

የወጣውን የመንገድ እሰታንዳርድ መነሻ ከማከናወን አንጻር በአንዳንድ ወረዳዎች ላይ ጉድለቶች መታየቸውን እና እቅዱን በሁሉም ቀበሌ  ተደራሸ አለማድግ፤ ከእስታንዳርድ በታች የመንገደ ከፈታ ማከናወን እና መንደርን ከመንደር ከማገናኝት ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ እና በቀጣይ በጀት ዓመት ማረም የሚገባቸው እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

በግበረ መልሱ መድረክ ላይ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳር  አቶ መንገሻ ፊታሞ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የአስተዳደር እና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ህብረት ቢያ የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡

ስኔ 18/2017 ዓ.ም 

ሀዋሳ፣ሲዳማ

newz11002

በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::

በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የሆነው ፊቼ ጫምባላላ የሰላም፣ የእርቅና  እና የአንድነት እሴቶች ጎልቶ የሚታይበት፣ የሲዳማ አባቶች ባማረና ባሸበረቀ የባህልና ስርዓት የሚያከናውኑት  እንዲሁም እንደ ሀገር  ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት የዘመን መለወጫ በዓል መሆኑ በፕሮግራሙ ተገኝተው በጋራ በተከበረበት ወቅት ተናግሯል።

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በUNESCO ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ በመሆን ከተመዘገበ ዘንድሮ አስረኛ አመቱን ያስቆጠረ ሲሆን በዉስጡ የያዘውን የባህል እሴቶቹን ይበልጥ ማሳደግ እና መንከባከብ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል ::

በዓሉን ስናከብር በአቅም የደከሙትንና በኢኮኖሚ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዜጎችን መርዳት የፍቼ ጫምባላል እሴት በመሆኑ ሁልጊዜ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቅሷል::

የፍቼ ጫምባላላ በዓል የባህል መገለጫ የሆኑት ጉዳዮች በተቋም ዉስጥ ጎልቶ መታየት የሚገባቸው አንድነት፣ ፍቅርና የሰላም  እሴቶች ይበልጥ በሴክተር ዉስጥ በቀጣይም ተጠናክሮ መጎልበት እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ መንከባከብ ሁሉም አመራር እና ሰራተኞች እንደሚጠቅባቸው በመልዕክታቸው ወቅት አበራርተዋል።

የመንገዶች ባለስጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ማቲዎስ በየነ በበኩላቸዉ የፍቼ ጫንባላላ በዓል ከጥንት ጀምሮ በአባቶቻችን ዘንድ ከነበረው እዉቀት ተደምሮ ከሲዳማ አልፎ የዓለም ቅርስ ወደ መሆን የደረሰ በዓል በመሆኑ በሴክተር ዉስጥ የሚገኙ ሰራተኞች እና አመራሩ በጋራ እሴቱን እና ባህሉን ይበልጥ እያማረ እንዲቀጥል መስራት ያስፈልጋል ብለዋል::

በመጨረሻም በዓሉን በማስመልከት በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይረክቶሬት በኩል የተዘጋጁ የጥያቄ እና መልስ እንዲሁም የምግብ ማጉረስና ሌሎች አዝናኝ ፕሮግራሞች ከሀልቾ የኪነት ቡድን ጋር በመሆን በደማቅ ሁኔታ ፕሮግራሙ ተከናውኗል::

መጋቢት 19/2017 ዓ.ም

ሐዋሳ፣ ሲዳማ

newz10222

ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::

ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::

p

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ የጉብኝት ቡድን በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን መነሻውን በማድረግ በወረዳዎች እየተሰሩ የሚገኙ የመንገድ ግንባታዎችን እና በሕብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎችን ምልከታ አድርገዋል ::

በምልከታቸውም በፌዴራል የመንገዶች አስተዳደር በኩል ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የአስፓልት መንገድ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል::

የመንገዱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ዉስጥ ከማከናወን አንፃር ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮች ተቀርፈው በጥሩ ሁኔታ ግንባታው መከናወን መጀመሩ እጅግ አበራታች እንደሆነ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል::

በሌላም በኩል በክልሉ መንግስት በመንገዶች ባለስልጣን እና በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸው እየተከናወኑ የሚገኙ መንገዶችን የጥገናና ግንባታ ሂደቶች ያሉበት ሁኔታ ምልከታ ተደርጓል::

በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ግንባታው እየተከናወ የሚገኘው የቦካሶ ዳዋሌ የ16 ኪሜ የመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክት ያለበት ደረጃ መመልከት ተችሏል::

የመንገዱ ግንባታ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በማድረግ ለአከባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ብዙ አስተዋፆ ያለው በመሆኑ በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተብራርቷል::

በተጨማሪም በሕብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉት የመንገድ ከፈታ ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች ላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል ::

በክልሉ በመንግስት በጀት ብቻ የመንገድ ግንባታን በማከናውን ሁሉንም ማህበረሰብ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተደራሽ  ማድረግ ስለማይቻል በሁሉም ዞኖች አመራሩ ትኩረት በመስጠት ሕዝቡን በማስተባበር የመንገድ ከፈታ እና የገጠር ኮሪደር ሥራዎችን መስራት እንደሚገባቸው ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምሮ ገልጸዋል ::

የቢሮው ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ በበኩላቸው በክልል ደረጃ በቢሮ በኩል እየተሰሩ ያሉት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እና ጥራት እንዲጠናቀቁ ከሁሉም የባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ህዝባችን ተጠቃሚ እንዲሆን እንሰራለን በማለት ተናግረዋል::

በጉብኝቱም የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አብርሃም ማርሻሎ የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞን አመራሮች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል ::

በቀጣይ በሌሎች ዞኖች የጉብኝት ፕሮግራሙ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል::

newz 10013

በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።

በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።

የቢሯችን አመራርና ሠራተኞች በጋራ በመሆን በዓለም ለ37 ጊዜና በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤችአይቪ/ኤድስን ቀን ” ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤችአይቪ/ኤድስ አገልግሎት ለሁሉም ” በሚል መሪ ቃልና እንዲሁም በዓለም ለ33ኛ ጊዜ ና በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀንን “የሴት ልጅ ጥቃት የኔም ነው ስለዚህ ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በጥምረት አክብረዋል።

መድረኩን የከፈቱት የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኮረኔል ሮዳሞ ኪአ በመልዕክታቸው:- የዛሬው ቀንን ስናከብር ኤችአይቪ/ኤድስና በሴቶችና ህፃናት  ፆታዊ ጥቃት የሀገራችንና የዓለም ችግር ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ስለሆነም ሁላችንም ቆም ብለን እራችንን በመመልከት የመከላከል ሀላፊነትና ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

 በክልሉ ጤና ቢሮ የኤችአይቪ/ኤድስ ሜንስቲሚንግ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት አሸናፊና በክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ የሥርዓተ – ፆታ ሜኒስቲሪሚንግ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት በቀለ አሁናዊ ሆኑ መረጃዎችን የሚያሳዩ ሰነዶችን አቅርበዋል።

በቀረቡት ሠነዶች ላይ አቅራቢዎቹ ያላቸውን ከፍተኛ ልምድና ብቃት በመጠቀም የበሽታውን ስርጭትና መስፋፋት እንዲሁም እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ትንኮሳ መድረኩን ባሳተፈ ውይይት በሳል ግንዛቤ ማስጨበጥ ችለዋል።

ከፍተኛ ባለሙያዎቹም ለተሳታፊዎች ይህ ችግር በሁላችችንም ቤት ሊከሰት የሚችል መሆኑን በመገንዘብ የዜግነት ግዴታና ሀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው የሚገኙ ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰብም የበሽታውን አስከፊነት በአካል ተገኝተው እንዴት መከላከል እንደሚቻል ተሞክሮአቸውን አስገንዝበዋል።

ተሳታፊዎች በመድረኩ ደስተኛ እንደሆኑና ወቅታዊ መረጃን በማግኘታቸው በመጠንቀቅ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠው መድረኩ ተጠናቋል።

ታህሳስ 2 ፣ 2017 ዓ.ም

ሐዋሳ፣ ሲዳማ