በመናኸሪያዎች እየተተገበረ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ (E-ticket) አገልግሎት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ተገለፀ።

በመናኸሪያዎች እየተተገበረ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ (E-ticket) አገልግሎት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ተገለፀ።

በሲዳማ ክልል በሚገኙ መናኸሪያዎች እየተሰጠ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ቀደም ሲል ምንም አይነት ህግ፣ ደንብና መመሪያ ያልተዘጋጀለት  እንደሆነ የገለፁት የቢሮ  ሀላፊው አቶ ጎሳዬ ጎዳና ናቸው።

የቢሮ ሀላፊው እንዳሉት የትራንስፖርት አገልግሎቱን በማቀላጠፍ፣ ተሣፋሪውን ከህገ ወጥ ክፍያ በማዳንና ከወንበር በላይ ባለ መጫን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት እስካሁን የህግ ማዕቀፍ ሳይበጅለት መቆየቱን በቁጭት ተናግረዋል።

ስለሆነም አሁን እየተዘጋጀ ያለው ህግ፣ ደንብና መመሪያ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩትን ተግዳራቶችንና የመናኸሪያዎችን መሠረተ- ልማት በማበልፀግ የሚጫወተው ሚና የጎላ እንደሚሆን በአፅንኦት አስረድተዋል ።

አክለውም ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢ- ቲኬቴንግ አገልግሎት በለሙት ሶፍትዌሮች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችም ተወዳዳሪ በመሆን የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል።

የዚህ ደንብና መመሪያ ዝግጅት ተደራጅተው የሚቀርቡትን ማህበራት ለማወዳደርና አሸናፊውን በትክክል ለመለየት ያስችላል።

የመናኸሪያዎችን ገፅታና መሠረተ ልማት በማሳደግ  የውስጥ ገቢያቸው እንዲጨምር የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል።

በውይይቱ እየተዘጋጀ ባለው ደንብና መመሪያ ላይ ገንቢ አስተያየታቸውን ያካፈሉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ እንዲሁም የቢሮው ማናጅመንት አካላት ናቸው።

ከመድረኩም መመሪያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ በሀዋሳ ከተማ በዞኖችና ወረዳ ከተማዎች በሚገኙ መናኸሪያዎች  ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሟል ።

መስከረም 27/2018 ዓ.ም

ሀዋሳ

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Comments are closed.