news 43

በባልፈው በጀት ዓመት በክልል ደረጃ 418 ኪሜ የመንገድ ጥገና የተከናወነ መሆኑ ተገለፀ ::

በባልፈው በጀት ዓመት በክልል ደረጃ 418 ኪሜ የመንገድ ጥገና የተከናወነ መሆኑ ተገለፀ ::

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በቢሮ የገጠር ቀበሌያት ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍ በኩል በስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች እንዲሁም ከማህበራት ጋር ምክክር ለማድረግ እና የተሻለ አፈፃፀም ላመጡት አካላት እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በሐዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አደራሽ እየተከናወነ ይገኛል::

news 51

የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ ::

የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ ::

የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም የሶስተኛ ቀን ፕሮግራም በቦርቻ ወረዳ በይርባ ከተማ እና በአለታ ጩኮ ወረዳ በጩኮ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀ “የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ቃል የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ዘሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል :::

የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በቀን 17/04/2015 አ. ም መነሻውን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በማድረግ በቦርቻ ወረዳ አስተዳደር አከባቢ እና በይርባ ከተማ,በአለታ ጩኮ ወረዳ አስተዳደር አከባቢ እና በአለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደር የመንገድ የትራፊክ አደጋ መከላከያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር እና ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የመን/ልማ/እና ትራ ፅ/ቤት ባለሙያዎች እና የፖሊስ ፅ/ቤት አካላት በጋራ በመቀናጀት ግንዛቤ ተሰጥቷል :

በአለታ ጩኮ ወረዳ አከባቢ እና በአለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደር በተሰራ ሥራ ተስፋ ሰጪ ለዉጦች እየመጡ ያሉ ቢሆን ባለ ሁለት ጎማ ሞተር ከልክ በላይ በመጫን እያደረሱ ያሉትን አደጋ በተቀናጀ መልኩ በመከላከል ማስቆም እንደሚገባ ለማየት ትችሏል ::

የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙም በቀጣይ ጊዜያት በሁለተኛ ዙር በተመሳሳይ ሁኔታ በተመረጡ ከተሞችና ወረዳዎች የሚቀጥል እንደሆነ ተጠቅሷል ::

news 61

የቡሉታ ደልድይ በዛሬዉ እለት የእስላብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ክልል የመንገዶች ባለስልጣን ገለፀ::

የቡሉታ ደልድይ በዛሬዉ እለት የእስላብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ክልል የመንገዶች ባለስልጣን ገለፀ::

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሆኮ ወረዳ አስተዳደር የቡሉታ ደልድይ በዛሬዉ እለት የእስላብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የሲዳማ ክልል የመንገዶች ባለስልጣን ገለፀ::

ከዚህ ቀደም ይህ ድልድይ ቶሎ ተገንብቶ ባለመጠናቀቁና በዲዛይን ምክንያት በመቆየቱ በአከባቢዉ በብዛት የምመረተዉን የቡናና ሌሎች የእርሻ ምርቶችንወደ ገቢያ ለማዉጣት አርሶ አደሩ እና የቡና ሳይት ባለሀብቶች ዉሃ እየሞላ ተሽከርካሪዎች ተሻግሮ መጫን በለመቻላቸዉ በሰዉ ኃይል ተሸክሞ ሲያሻግሩ አርሶ አደሩና ነጋደዉ ለሌላ ተጨማሪ ዉጪ እና ለከፍተኛ እንግልት ሲዳረግ እንደነበሩ ተጠቅሷል ::

ድልድዩ አሁን ወደ ማጠናቀቁ እየደረሰ በመሆኑ የአከባቢዉ ማህበረሰብ እጅግ ደስተኞች እንደሆኑ ገልፆዋል ::

የድልድዩም ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ህዝቡ አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል ::