የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልል ደረጃ እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ::
ርዕሰ መስተዳድሩ ጉብኝት ያደረጉት በክልሉ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ፣ በመንገዶች ባለስልጣን እና በቢሮው ዩራፕ ዘርፍ የተሰሩ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን ነው::
በጉብኝቱም የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ምክትል ፕሬዘደንት ክቡር አቶ በየነ ባራሳ፣ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አመራሮች፣ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እና የማናጅመንት አባላት ተገኝተው እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል::
በበጀት ዓመቱ በዩራፕ ዘርፍ የግንባታ ፕሮጀክቶች 26 የመንገድ ፕሮጀክቶች 153.5 ኪሜ እንዲሁም የጥገና ፕሮጀክቶች 28 መንገድ 198 ኪሜ በክልሉ መንግስት በጀት ተይዞላቸው እየተገነቡ የሚገኙ መንገዶች ተጎብኝቷል::
በበጀት ዓመቱ ሁሉም ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እቅድ ተይዞ እየተሰሩ እንደሆነ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በመስክ ምልከታ ወቅት ገልጸዋል::
በጉብኝቱም ወቅት የመንገድ ስራዎች በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች ጥራታቸዉ ተጠብቆ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ሁሉም አካላት መረባረብ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ገልጸዋል::
ጥር 7 /2016 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::