የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ተመስገን ተረፈ ከሴክተሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ በቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ምክክር አደረጉ::

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ተመስገን ተረፈ ከሴክተሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ በቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ምክክር አደረጉ::

በትውውቅ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኢንጅነር ተመስገን ተረፈ የተቋም ግንባታ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን እንደሆነ ገልጸዋል::

የተቋም ግንባታን በቴክኖሎጅ በማስደገፍ ለተገልጋዮች ምቹ የሆነ አከባቢን በመፍጠር ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥበት እንዲሆን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግሯል::

በትራንስፖርት ዘርፍ የመጣውን ለውጥ ይበልጥ ማጠናከርና አገልግሎትን የማዘመን ተግባራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር እንደሚሰራ አብራርቷል::

የመንገድና የድልድይ ግንባታዎች እንድሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ በማድረግ ጥራትና ተደራሽነት ላይ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል::

የቢሮ ሰራተኞች በበኩላቸው ከሰራተኞች ጋር አመራሩ ግልፀኝነት በመፍጠር የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመስራት ሰራተኞች ለተቋም ግንባታ ሚናቸው በሚገባ እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል::

በሌላም በኩል የበጀት ዓመቱ ስራዎች ሁሉንም ሰራተኞችን አሳታፊ በማድረግ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ሥርዓት በመዘርጋት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::

በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ተመስገን ተረፈ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ሴክተሩን ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ለመቀየር የተግባርና አስተሳሰብ አንድነትን በማጠናከር ተቋሙ የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል::

አንድነታችን ከተጠናከረ የክልሉን ማህበረሰብ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ ተናግረው መድረኩ ማጠቃለያ ተደርጓል::

የቢሮ ሠራተኞችም ለአዲሱ የቢሮ ኃላፊ ቀጣዩ የሥራ ዘመን የስኬት እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል::

በትውውቅ መድረኩ ላይ የቢሮና የመንገዶች ባለስልጣን የማናጅመንት አባላት ፣ የዳዬ ድስትሪክት ማናጅመንት አባላት እንዲሁም የሴክተሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::
==============================

መስከረም 27/01/2019 ዓ.ም
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሐዋሳ, ሲዳማ

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Comments are closed.