በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጳጉሜ 1 የአገልግሎት ቀን በክልል ደረጃ በሁሉም መናሃሪያዎች ዉስጥ ተከበረ::
በመረሃ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል የሪኦተ ዓለም እና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አስፋው ጎኔሶ እንዲሁም የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንትባ ክቡር መኩሪያ ማርሻዬ እንዲሁም የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት የትራንስፖርት ማህበራት ተሳፋሪዎች እና አሽከርካሪዎች በተገኙበት የጳጉሜ 1 ቀን የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በክልል ደረጃ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በአሮጌ መናሃሪያ እየተበረ በሚገኘው ፕሮግራም ላይ የታክስ አግልግሎት ከ12 ሰዓት ጀምሮ ነፃ እንደሆነ እና ሁሉም ተሽከርካሪ በጥንቃቄ አገልግሎት እንዲሰጡ እና በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰዉን ሞት በጋራ ሁሉም የባለ ድርሻ አካላት መከላከል እንደሚገባ የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አስፋው ጎኔሶ ግልፆዋል ::
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በበኩላቸዉ በዛሬ ዕለት ሁሉም አሽከርካሪዎች የሚሰጡትን አገልግሎት ህዝብን ባማከለ እና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል::
በእለቱ አሽከርካሪዎች, የማስልጠኛ ተቋማት የህግ አስከባሪዎች እንዲሁም ተሳፋሪዎች ቃል መሃላ በመግባት ማጠቃለያ ተደርጓል::
ጳጉሜ 1/2015 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::