ትላንት በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተሰማራው የቁጥጥር ግብረ-ኃይል ሥራ ዛሬ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቀጥሏል
ከክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ እንዲሁም ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተውጣጣው ግብረ-ኃይል ሥራ የመርሃ-ግብሩ የቴክኒክ ቁጥጥር ቡድን በተገኙበት ተጀምሯል።
ዛሬ ማለዳ በተጀመረው በዚህ መርሃ-ግብር ግብረ-ኃይሉ በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችና መውጫ መስመር ባሉ ዋና ዋና የመንገድ አውታሮች ላይ ጥብቅ የቁጥጥርና ሕግ የማስከበር ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል።
በምልከታውም በዞኑ ሕጋዊ ሆኖ ከማሽከርከር አንጻር ብዙም የሕግ መተላለፎች እንዳልታዩ የቁጥጥር ሥራው ኮሚቴ መረጃ ይጠቁማል።
በሁለት ቡድን የተሰማራው የቁጥጥር ግብረ-ኃይል በወጣው መርሃ-ግብር መሠረት በቀጣይ ቀናትም በሁሉም ዞኖች ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
የትራፊክ አደጋን መከላከል የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ ይጠይቃል!
የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት እያካሄደ የቆየው የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር ሥራ ግብረመልስ ተገመገመ
ትላንት በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተሰማራው የቁጥጥር ግብረ-ኃይል ሥራ ዛሬ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቀጥሏል
የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ተመስገን ተረፈ ከሴክተሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ በቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ምክክር አደረጉ::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::