የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ጉበኝት አደረጉ ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ጉበኝት አደረጉ ::

በዛሬም የመስክ ጉበኝት የቢሮ አመራሩ ከቦርጃ ውጅግራ ፕሮጀክት የ5.56 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን የፕሮጀክት ስራዎች ያለበትን ለማየት ተችሏል:: በጉብኝቱም የመንገዱ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለማየት ችለናል::

የመንገዱ መገንባት የማልጋ እና የወንዶ ገነት ወረዳን የሚያገናኝ በመሆኑ ለአከባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እጅግ በጣም ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መንገድ እንደሆነ በምልከታ ወቅት ለማረጋገጥ ችለናል::

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ዉስጥ እስከ ጥር 30/04/2016 ዓ. ም ድረስ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ የእስታር የሥራ ተቋራጩ አስተባባሪዎች አሳውቋል:: ፕሮጀክቱ በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቅ የቢሮ ማናጅመንት አመራሩ በቅርበት ክትትል እንደሚያደርጉ ገልፃዋል::

ታህሣስ 18፣ 2016 ዓ. ም 

ሐዋሳ, ሲዳማ

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Comments are closed.