የአከባቢና ማህበራዊ ክዋኔ ኦዲት በተቀናጀ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ተገለፀ::
በሲዳማ ክልል በRCFSP ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ በሲዳማ ክልል የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በኩል የ2017 በጀት ዓመት የአከባቢ እና ማህበራዊ ጉዳዮች አጠባበቅ ዙሪያ የተከናውኑ ተግባራት የክዋኔ ኦዲት ግምገም ሪፖርት የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና በተገኙበት ተገምግሟል::
ፕሮግራሙ በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ በመሆኑ ሁሉም ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው በመድረኩ ተገልጿል::
በግምገማው በቀረበዉ የክዋኔ ኦዲት የመንገዶች እና ስየአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን መንገዶችን ስፔሻል እስትራክቼሮች በአጠቃላይ ወደ 66% የሚሆኑትን በመለየት ኦዲት እንደተደረገ ከሪፖርቱ ለመመልከት ተችሏል::
በፕሮግራሙ የአከባቢ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን ላይ ትኩረት በማድረግ በአንዳንድ አከባቢዎች በማህበረሰቡ ላይ ተፅእኖ የምፈጥሩ ጉዳዮች ተለይቶ በቀጣይም ኦዲቱን መነሻ ተደርጎ ጠንካራ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተብራርቷል::
የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን ጋር በቅርበት በመስራትየሚታዩ ችግሮችን እየለዩ ማረም የሚገባዉ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽታዬ ዩሙራ ተናግረዋል::
የመንገድ ጥራትን እና ስታንዳርድ በዓለም ባንክ የወጣዉን መነሻ በማድረግ በአከባቢ እና ማህበረሰብ ደረጃ ጉዳት እንዳያደርሱ መስራት እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል::
በክልል ደረጃ ተገባራዊ እየተደረገ የሚገኘዉ ፕሮግራም ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በቢሮ በኩል እንዲሁም በፕሮግራም ሰራተኞችና በባለድርሻ አካላት በኩል ጠንካራ ቅንጅት ተፈጥሮ እየተሰራ መሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ተብሏል::
በክልል ደረጃ የማተሪያል ማምረቻ ቦታዎች መልሶ በማልማት ለሌላ አደጋ እንዳይዳረግ ፕሮጀክቶችን እየሰሩ የሚገኙ ኮንትራክተሮች መልሶ በማልማት ማህበረሰቡን ከአደጋ እንዲሁም አከባቢውን ከጉዳት መከልከል ላይ ትኩረት እንዲደረግ በሰነዱ ተብራርቷል::
የቢሮ ኃላፊ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ፕሮግራሙ በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተደረገ የሚገኝ በመሆኑ ጥራት ያለውን ሥራ በመስራት በሰባቱም ወረዳዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል::
በመጨረሻም በክልሉ የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በክዋኔ ኦዲት በኩል የተለዩ ጉድለቶችን ጊዜ ሳይሰጥ ማረም እንደሚገባ ገልጸዋል::
በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት በጋራ ተግባሩን እየገመገሙ ጠንካራ የኦዲት ሥራዎች እየተሰሩ ህዝባችን በፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይበልጥ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ ባለመሆኑ ቅንጅቱን ማጠናከር እንዲሁም በቀሪ ወረዳዎች ፕሮጀክቶች ባሉበት ትኩረት በመስጠት ከአመራራና ከኮንትራክተሮች ጋር በቅርበት ቼክ ሊስትን በማዘጋጀት መስራት እንደሚያስፈልግ የቢሮ ኃላፊ አቅጣጫ አስቀምጧል::
በመድረኩ የቢሮ አመራሮች;የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽታዬ ዩሙራ; የፕሮግራሙ ሠራተኞች እና በኦዲት ሥራ ላይ የተሳተፉ ሠራተኞች ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል::
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ህዳር 08, 2018 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ




