በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የሆነው ፊቼ ጫምባላላ የሰላም፣ የእርቅና እና የአንድነት እሴቶች ጎልቶ የሚታይበት፣ የሲዳማ አባቶች ባማረና ባሸበረቀ የባህልና ስርዓት የሚያከናውኑት እንዲሁም እንደ ሀገር ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት የዘመን መለወጫ በዓል መሆኑ በፕሮግራሙ ተገኝተው በጋራ በተከበረበት ወቅት ተናግሯል።

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በUNESCO ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ በመሆን ከተመዘገበ ዘንድሮ አስረኛ አመቱን ያስቆጠረ ሲሆን በዉስጡ የያዘውን የባህል እሴቶቹን ይበልጥ ማሳደግ እና መንከባከብ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል ::

በዓሉን ስናከብር በአቅም የደከሙትንና በኢኮኖሚ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዜጎችን መርዳት የፍቼ ጫምባላል እሴት በመሆኑ ሁልጊዜ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቅሷል::


የፍቼ ጫምባላላ በዓል የባህል መገለጫ የሆኑት ጉዳዮች በተቋም ዉስጥ ጎልቶ መታየት የሚገባቸው አንድነት፣ ፍቅርና የሰላም እሴቶች ይበልጥ በሴክተር ዉስጥ በቀጣይም ተጠናክሮ መጎልበት እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ መንከባከብ ሁሉም አመራር እና ሰራተኞች እንደሚጠቅባቸው በመልዕክታቸው ወቅት አበራርተዋል።

የመንገዶች ባለስጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ማቲዎስ በየነ በበኩላቸዉ የፍቼ ጫንባላላ በዓል ከጥንት ጀምሮ በአባቶቻችን ዘንድ ከነበረው እዉቀት ተደምሮ ከሲዳማ አልፎ የዓለም ቅርስ ወደ መሆን የደረሰ በዓል በመሆኑ በሴክተር ዉስጥ የሚገኙ ሰራተኞች እና አመራሩ በጋራ እሴቱን እና ባህሉን ይበልጥ እያማረ እንዲቀጥል መስራት ያስፈልጋል ብለዋል::


በመጨረሻም በዓሉን በማስመልከት በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይረክቶሬት በኩል የተዘጋጁ የጥያቄ እና መልስ እንዲሁም የምግብ ማጉረስና ሌሎች አዝናኝ ፕሮግራሞች ከሀልቾ የኪነት ቡድን ጋር በመሆን በደማቅ ሁኔታ ፕሮግራሙ ተከናውኗል::
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ፣ ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::