በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የ2017 ዓ.ም ሀገራዊ የተቀናጀ ድንገተኛ የቁጥጥርና ግንዛቤ ሥራ ከፌዴራል መንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም ከሀዋሳ ከተማ አስተዳዳር ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል ::

የቁጥጥር ሥራ በተመረጠው የቁጥጥር ቱላ ክፍለ ከተማ ገመጦ ወንዶ ገነት መታጠፊያ አከባቢ፤ እንዲሁም ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ጨኮ ወረዳና ከተማ አስተዳደርና ዳራ ቀባዶ ወረዳ መጪሾ አከባቢ መስመር ከሁለቱም ዞን፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ጎልተው የታዩ ደንብ መተላለፊያዎች ላይ ቁጥጥር ተደርጓል ::

በተደረገው የተቀናጀ ቁጥጥር ወቅት የደህንነት ቀበቶ አለማሰር፣ የቴክኒክ ምርመራ ቦሎ አለማደስ፣ 3ኛ ወገን አለመግባት፣ ትርፍ ተሳፋሪ መጫን፣ ያልተፈቀደ እስቲከር መለጠፍ፣ ያለ መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር እንዲሁም በተለያዩ ደንብ መተላለፎች ላይ ያተኮረ የቁጥጥር ሥራ ተሰርቷል::

በዕለቱ በተሰራው የቁጥጥር ሥራ በአጠቃላይ 431 ተሽከርካሪዎች የታዩ ሲሆን፡ ከነዚህ ውስጥ ደንብ ተላልፈው የተገኙ 56 አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የህግ ማስከበር እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ታውቋል:: ከደንብ ተላላፊዎች ብር 57,500 (ሃምሳ ሰባት ሺ አምስት መቶ ብር) ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ወቅት የተወሰነ ክፍተት ያለባቸው አሽከርካሪዎች 375 የሚሆኑት በቀጣይ እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት 850 ለሚሆኑ ተሳፋሪዎችና ለ100 ባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል:: የተቀናጀው ቡድን የቁጥጥር ሥራ በቀሪ ቀናት በተለዩ ቦታዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
24/03/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ፥ ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::