በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጥና የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
ከክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ፤ከክልሉ ጠቅላይ ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም በየደረጃው ካሉ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በክልላችን በተመረጡ ቦታዎች በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአሮጌው መናኸሪያ ውስጥ :- የሶስተኛ ወገን፣ የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ቦሎ፣ የስምሪት ሂደት ፣የተሳፋሪ የትኬት አቆራረጥና መውጫ አሰጣጥን አስመልከቶ እንዲሁም በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ መናኸሪያ ዉስጥ ቁጥጥር ተደርጓል:: የቁጥጥርና የተቀናጀ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን በቁጥጥር ወቅት ጎልተው የታዩ ደንብ ተላላፊዎች በህጉና በደንቡ መሠረት ተገቢው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ፡፡
የተቀናጀውን የቁጥጥር ቡድን በየደረጃው ሥራውን ያለበት ሂደትና ያጋጠሙ ችግሮችን ከሁለቱም መዋቅር ጋር በመሆን ጎን ለጎን በመገምገም በቦታው እየተፈታ መሄድ እንዳለበትና የቁጥጥር ተግባሩ አጠናክሮ በማስቀጠል የህግ ማስከበርና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
የተቀናጀው የቁጥጥር ቡድን በቀጣይም በሌሎችም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚቀጥል ይሆናል ።
የካቲት 11 /2016 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::