በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በሀገር ደረጃ ያጋጠመውን የታርጋ እጥረትን መነሻ በማድረግ በክልሉ በሐዋሳ ከተማ እና በዞን ከተሞች የኤሌክትሪክ ታክሲ እንዲሁም ኩይት ተሽከርካሪዎችን በመግዛት በመንግስት በኩል ምላሽ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ እንደሆነ በመድረኩ በቢሮ ኃላፊ ተገልፆዋል:: ለዚህም ምላሽ ከቢሮ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጨምሮ አብራርቷል ::
ቢሮው እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመሆን ባደረገው ጥረት ጊዜያዊ የስምሪት ኮድ ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ኮድ መዘጋጀቱን በተዘጋጀው መመሪያ እና በማስፈፀምያ አቅጣጫ ላይ በቀረበው ሰነድ ተመላክቷል::
የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና በመድረኩ እንደተናገሩት ዜጎች ላይ እየደረሰ የሚገኘዉን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ጊዜያዊ ስምሪት ኮድና የድጋፍ ደብዳቤ ተሰጥተው ጊዜያዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ ታሳቢ የተደረገ እንደሆነ አብራርቷል::
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር ተስፋዬ ደብሶ በበኩላቸዉ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥሩን የተሳለጠ ለማድረግ ቢሮው ከባለ ድርሻ ጋር በመቀናጀት ጊዝያዊ መፍትሄ ለዜጎች ለመስጠት መመሪያ በማዘጋጀት ችግሮች እንዲፈቱ ማድረግ መቻሉን ገልፆዋል::
መመሪያው በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲጠናቀቅ የተሰራው ሥራ አበራታች መሆኑ የገለፁት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል በቀጣይ ተግባራዊ ሲሆን ተጨማሪ ማሻሽያ የሚፈልጉ ጉዳዮች እየታዩ የሚስተካከሉ እንደሆነ ተናግሮ አስፈፃሚ አካላት ዝርዝር ጉዳዮችን ወደ ተግባር መቀየር እንደሚገባቸውና ህገ ወጥ ድርጊት በምፈፅሙት ላይ ተፈፃም እንዲደረግ አሳስቧል::
የወጣው መመሪያ በክልል ደረጃ ለሦሶት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፆዎ የሐዋሳ ከተማና የዞን የፖሊስ አስተባባሪዎች የወጣውን መምሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል::
በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ እንዲሁም በሁሉም የዞን ከተሞችና ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ታክሲ እንዲሁም አዳድስ በነዳጅ የሚሰሩ ታክሲዎችን የገዙ ዜጎች ቢሮ በመምጣት አስፈላጊ መረጃ በመያዝ እየተመዘገቡ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቅሷል::
የጊዜያዊ የስምሪት ኮድ መመሪያ ቁጥር 43/2018 በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እንዲሆን መደረጉ ተገልፆዎ በቢሮ ኃላፊ በክቡር ጎሳዬ ጎዳና በኩል ፀድቆ ከነገ ከቀን 15/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ በክልል ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል::
በቢሮ በኩል ታትሞ የተዘጋጁ ጊዜያዊ የስምሪት ኮድ ስርጭት በቢሮ ብቻ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ሕጋዊ መረጃ እያቀረቡ ከትራንስፖርት ዘርፍ የተሽከርካሪ ዳይሬክቶሬት እንዲወስዱ ተግባቦት ላይ ተደርሷል::
በመድረኩ የቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ; የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር ተስፋዬ ደብሶ የቢሮ ማናጅመንት አባላት ; የርእሰ መስተዳድር የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ; የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሕግ ባለሙያዎች ;የሐዋሳ ከተማና የዞኖች መምሪያ ኃላፊዎች;የፖሊስ አዛዥች እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::
================================
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሐምሌ, 2018 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ::