ለተቋማት የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል።
የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ከሴክተሩ አመራርና ባለሙያዎች ትውውቅ ጋር አድርገዋል።
በትውውቅ መድረኩ የቢሮ ሀላፊው በመልዕክታቸው:- በቀጣይ የሚኖረን የስራ ዘመን ለተቋሙ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራትን ቀልጣፋ እናደርጋለን፣ ቀደም ሲል የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በማጎልበት ባሉት ጉድለቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ርብርብ ይደረጋል፣ የምንሠራው ሥራ ብዙሀንን ማከለ መሆን አለበት ብለዋል።
አክለውም የተቋሙ ሠራተኞች ምቹ ውጤታማ ማድረግና ሠላማዊ የሆነ የሥራ ግንኙነት መፍጠር ይገባል። እንዲሁም ለባለሙያው የሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎእንዲሰጡና ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲዘምን አስፈላጊው ጥረት ሁሉ ይደረጋል በማለት አመላክተዋል።
ከዞንና ወረዳዎች ጋር የሚኖረው ዲፕላማሲያዊ ግንኙነትና ትስስር የበለጠ እንደሚጠናከር ተገልጷል።
በመድረኩም የእንኳን ደህና መጣህ የኬክ ቆረሳ መርሀ – ግብር ተከናውኗል ።
በልማት ልቅድ ዳይሬክተር አማካኝነት የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም እቅድዋና ዋና አቅጣጫዎች ሠነድ በመድረኩ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል ።
ከተሣታፊዎች ያለፋትን ጉድለቶች የሚያርሙና በቀጣይ ጠንክሮ ከሀላፊው ጋር አብሮ ለመስራት የሚያችሉ አስተያየቶች ተሠጥተዋል።
በፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ፍጥነት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ጠንካራ ቅንጅዊ አሰራርን በመዘርጋት በክልሉ በመንገድ እና ድልድይ ግንባታዎች በኩል የሚታዩ ችግሮች ትኩረት ተሰጥተው እንደሚሰራ ገልፆል::
በመጨረሻው ሀላፊው መድረኩን ሲያጠቃልሉ:- የተነሱትን ሀሳቦች በመገንዘብ በቀጣይ የሚኖረን የሥራ ዘመን መልካም የሥራ ግንኙነት ፈጥረን የተቋሙን ገፅታ በመቀየር አገልግሎነት አሠጣጡን ለማሳደግ የሚቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል።
መልካም የስኬት ፍሬ የምናፈራበት የብልፅግንና ዘመን እንሆንልን እመኛለሁ በማለት መድረኩ ተጠናቋል።
መስከረም 28 / 2018 ዓ.ም
ሀዋሳ
የዘገበው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው!
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳና የዘመነ የአመራርና ባለሙያዎች ትጋት ለተቋም ግንባታ ቁልፍ እንደሆነ ተገለፀ::
ለተቋማት የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል።
በመናኸሪያዎች እየተተገበረ ያለው የኢ- ቲኬቲንግ (E-ticket) አገልግሎት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ተገለፀ።
በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የRCFSP ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ::
የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ::