ስለ እኛ
ለክልሉ ሕብረተሰብ የተቀናጀ ልማት ለማምጣት የሚያስችሉ የተለያየ ደረጃ ያላቸው መንገዶችን በማስጠናት፣ በመገንባት፣በመጠገንና በማስተዳደር በመላው ሕብረተሰብ ጉልበት፣ ገንዘብ፣ ዕውቀትና ቁሳቁስ ሰፊ ተሳትፎ የሚሰሩ ሁሉ አቀፍ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ፕሮግራምን በልዩ ትኩረት ተፈፃሚ በማድረግ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማስፋፋትና በማጠናከር፣ የአሽከሪካሪና ተከሽከሪካሪ ብቃትን በማረጋገጥ እና የህብረተሰቡን የመንገድ አጠቃቀም የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤን በማሳደግ የትራንስፖርት ተጠቃሚነትን እና ደህንነትን እውን ማድረግና መላውን ሕዝብ አደራጅቶ በማነቃነቅ በሴክተሩ እቅዶች አፈፃፀም ውጤት ላይ ማሳተፍ፡፡
የክልሉ ሕብረተሰብ ወደ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ማዕከላትና የአገልግሎት ተቋማት የሚያደርስ በቂ፣ ምቹና አስተማማኝ የመንገድ አውታርና የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡
ጥራት፣ግልጽነት፣ተጠያቂነትና ፍትሀዊነትን ጥምር የሴክተራችን ሀብቶች እናደርጋቸዋለን፡፡ ቀልጣፋ አገልግሎትና ውጤታማነትን ማረጋገጥ የተግባራችን ስኬት መለኪያዎች ናቸው፡፡ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ ልማት ላይ እናተኩራለን፡፡ ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን፡፡ በጋራ እንሰራለን ስኬቱም ውድቀቱም የጋራችን ነው፡፡ የሙያ ስነ-ምግባር መጠበቅ መለያችን ነው፡፡ ለተገልጋዮቻችን እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡ ውጤት ይሸለማል፡፡
የክልሉ መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን ባወጣው አዋጅ መሠረት የትራንስፖርት ቢሮ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
- በክልሉ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲስፋፋ ያደርጋል፣
- የትራንስፖርት አገልግሎቶች አቅርቦት በተቀናጀ መንገድ የክልሉን የልማት ስትራተጂዎች በሚያሟ ሁኔታ እንዲያገለግል መደረጉን ያረጋግጣል፣
- የትራንስፖርት አገልግሎቶች አስተማማኝና ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት እንዲዘረጋና ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
- በሀገርቱ የትራንስፖርት ፖሊስዎች መሠረት በክልሉ የሚገኙ ውሃ አካላት ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስፋፋ ያበረታታል፣ድጋፍ ይሰጣል፣
- በክልሉ የትራንስፖርት መሠረተ-ልማት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣እንዲሻሻልና እንዲጠገን ያደርጋል፣
- በክልሉ ውስጥ በሕዝብ ማመላለሻ ንግድ ለሚሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ፈቃድ ይሰጣል፣በዘርፉ የሚቋቋሙ ማህበራትን ይመዘግባል፣የነፃ ስምሪት አሰራር አፈፃፀምን ይቆጣጠራል፣ይሰርዛል፣
- የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና እና የቴክኒሻኖች ማሰልጠኛ ማዕከላት ያቋማል፣ ስልጠና ለሚሰጡ የቴክኒክ ምርመራ ለማያደርጉ ሰዎች ፈቃድ ይሰጣል፣ይቆጣጠራል፣ ሥልጠና ይሰጣል፣በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ያደርጋል፣
- የህዝብና የጭነት ማመላለሻ መናሄርያዎች እንድቋቋሙ ያደርጋል፣ያስተዳድራል፤
- የመንገድ ትራንስፖርት ሕጎች ያስከብራል፣የመንገድ ታራፊክ ደህንነት ይቆጣጠራል፣ይከታተላል፣
- ትራንስፖርትን የሚመለከቱ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ያጠናቅራል፣ለሚመለከታቸው አካላት ያስተላልፋል፣
- በክልሉ የመንገድ ደህንነት ፈንድና ካውንስል ያቋቁማል፣