ከፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር ምክክር ተደረገ::

ከፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር ምክክር ተደረገ::

በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው  የRCFSP ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ በክልሉ በፕሮግራሙ የታቀፉ የባለድርሻ አካላት በሙሉ በተገኙበት ከድጋፍ እና ክትትል ቡድን ጋር  ውይይት ተደርጓል ::

የድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ የነበሩ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች ተለይቶ እንዲሁም የ2018 በጀት በሚሰሩ ፕሮጀክቶች አንፃር ትኩረት በማድረግ ሠነድ በድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ ቀርቧል::

በመድረኩ የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት ፕሮግራሙ በክልላችን በ7 የተመረጡ ወረዳዎች ተግባራዊ እየሆነ ያለ በመሆኑ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በማከናወን ዉጤታማ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል ::

ከፌደራል የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች በክልሉ ያለው የ2017 በጀት ዓመት የተሻለ ዉጤት የመጣበት ክልል በመሆን ሁለተኛ ወጥቶ እዉቅና ያገኘ ክልል እንደመሆኑ በ 2018 በጀት ዓመት የተያዙ ፕሮጀክቶችን በሙሉ ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ለማድረግ በጊዜ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል::

በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ ፕሮግራም እንደመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት የሚጠበቅ መሆኑ ተገልፆ አማካሪዎች እና ኮንትራክተሮች  አቅማቸውን ሙሉ እንዲጠቀሙ ከማድረግ አንፃር ጠንካራ ቁጥጥር ከማድረግ ረገድ የሚታዩ ችግሮች በዚህ በጀት ዓመት ልታረሙ እንደሚገባ ተገልጿል::

በመድረኩ የተገኙት የባለድርሻ አካላት ይሄ ፕሮግራም በክልሉ የታቀፉ ወረዳዎች የመንገድ ግንባታና ጥገና እንዲሁም የድልድይ ግንባታዎች ማህበረሰብን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ አስፈላጊ ድጋፍ  እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::

የቢሮ ኃላፊ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ከዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ ፕሮግራም በመሆኑ የፌደራል የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በቅርበት ድጋፍ እና ክትትል እንዲያደርጉ እና በክልል ደረጃ የተደራጀዉ የስትሪንግ እና የቴክኒክ ኮሚቴ በየጊዜው እየተገመገመ እንደሚመራ ተናግረዋል::

በመጨረሻም ባለፈው ዓመት ተግባራዊ ሲደረጉ የነበሩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በቢሮ በኩል ጠንካራ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የሚመጣውን በጀት እና ድጋፍ ለታለመለት አላማ ለማዋል በ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል::

በድጋፋዊ ክትትልና  ምክክር መድረክ ላይ የቢሮ አመራሮች ፣ የፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የድጋፍ ቡድን ፣ የግዥ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፣ የአከባቢ እና አየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን ኃላፊ ፣ የክልሉ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፣እንዲሁም የሪካፕ ፕሮግራም አስተባባሪ ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል::

ህዳር 02/2018 ዓ.ም 

Hawaasa, Sidaama

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Tenne Odoo Iillishshe

Comments are closed.