ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳና የዘመነ የአመራርና ባለሙያዎች ትጋት ለተቋም ግንባታ ቁልፍ እንደሆነ ተገለፀ::
ለሴክተሩ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደዋል።
ቢሮ ሀላፊው ሲናገሩ :- የቢሯችን አመራርና ባለሙያዎች ከብልሹ አሠራርና የሠራተኞችን አዋጅ ደንብና መመሪያን በአግባቡ ከመተግበር አንፃር ምን እንደምንመስል ራሳችንን ለመመልከት ይረዳን ዘንድ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል።
አክለውም አቶ ጎሳዬ ይህ መድረክ ሁላችንም ብልሹ አሠራርን እንድንጠየፍና የሠራተኞች አዳዲስ የወጡ አዋጆች: ደንቦችና መመሪያዎች ያለንን ግንዛቤ በማሳድግና ግልፀኝነት በመፍጠር ድርሻው የጎላ እንደሚሆን እምነቴ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም በተቋሙ ሊከሠቱ የሚችሉ ብልሹና ተገቢ ያልሆኑ አሠራሮችን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለማቀጨጭ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ ይደረጋል ሲሉ አስገንዝበዋል ።
በመድረኩ ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በአዳዲስ አዋጆች ላይ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሠራርን አስመልከቶ ደግሞ ከፀረ- ሙስና ኮሚሽን በተጋበዙ አሠልጣኞች የሥልጠና ሠነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ከተሣታፊዎችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ከመድረክ ምላሽ ተሠጥባቸዋል።
በመጨረሻም ከመድረኩ በቀጣይ ለሚኖሩን ተግባራት በአመራሩና ባለሙያዎች መካከል ጠንካራ ቲም እስፕሪት በመፍጠርና ግልፀኝነት በማጎልበት በዕቅድ በመመራት ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ከስምምነት በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል ።
ጠንካራ የአመራር ሥርዓትና የባለሙያዎች ትጋት የተቋምን ገፅታ ይቀይራል!!
ጥቅምት 2018 ዓ.ም
ሀዋሳ
Muli Yanna Odoo
የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት እያካሄደ የቆየው የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር ሥራ ግብረመልስ ተገመገመ
ትላንት በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተሰማራው የቁጥጥር ግብረ-ኃይል ሥራ ዛሬ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቀጥሏል
የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ተመስገን ተረፈ ከሴክተሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ በቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ምክክር አደረጉ::
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::