የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ::

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በክልል ደረጃ እየደረሰ ያለዉን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሂዷል::
የምክክር እና ስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የመንገድ ደህንነና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኮሮነል ሮዳሞ ኪአ እንደተናገሩት በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተናግሯል::

በሲዳማ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት ከ 2014 እስከ 2017 ድረስ ብቻ 474 ዜጎች በሞትእና 313 ዘጎች ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን እና ከ 30 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ንብረት መዉደሙን ገልፆዋል::
በሌላም በኩል በ 2017 በጀት ዓመት ብቻ ወደ 180 ዜጎች በመንገድ ትራፊክ አደጋ የሞት አደጋ የደረሰባቸው እንደሆነ አስረድቷል::
በተጨማሪም በክልል ደረጃ 89.9 % አደጋ እየደረሰ ያለዉ ከተፈቀደው ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከሩ መንስኤ መሆኑን ጠቅሰዉ አስከርካሪዎች ለዚህ ሚናቸው ከፍተኝበመሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል::

የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት በብቃት በማሰልጠን ኃላፊነታቸዉን በመዎጣት መንግስት ያወጣዉን ደንብ እና አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ እንዲወጡ አሳስቧል::
በክልል ደረጃ ለትራፊክ አደጋ መከሰት መንስኤ ከሆኑት ጉዳዮች ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት, አሽከርካሪዎች ደንብን አለማሽከርከር ለትራፊክ አደጋ መከሰት ምክንያት መሆኑን ገልፆዋል::

በሌላም በኩል የተሽከራካሪ ብቃት ማረጋገጫ ተቋማት በቃት ሌላቸው ተሽከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት የሚታዩ ችግሮች መሆኑ ተነስቷል::
በምክክሩ መድረክ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት የሚደርሱ የመንገድ ትራፊክ አደጋን የመከላከል ጉዳይ ለመንግስት አካላት ብቻ የሚተዉ ሳይሆን የማሰልጠኛ ተቋማት, የትራንስፖርት ማህበራት የቴክኒክ ምርመራ እንዲሁም ኢንሹራንሶች አደጋዉን ለመቀነስ ሚናችን ትልቅ በመሆኑ ግዴታቸንን እንወጣለን በማለት ገልፆዋል::

በመጨረሻም የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኮሮነል ሮዳሞ ኪአ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሬ ሪቂዋ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል::
በምክክር መድረኩ ላይ የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች የክልል ፖሊስ ኮሚሽን, የሐዋሳ ከተማ የመ/ል/ት/መምሪያ ኃላፊዎች የ ትራንስፖርት ማህበራት,የማሰልጠኛ ተቋማት, እንሱራንሶች እንዲሁም የባለድርሻ አካላት በሙሉ ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል::
ነሐሴ, 2017 ዓ.ም ሐዋሳ
Muli Yanna Odoo
የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ::
በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የህብረተሰብ ተሳትፎ ሥራ ድጋፍ እና ክትትል ግብረ መልስ ተሰጠ፡፡
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።