nez1

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላክያ የአብይ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላክያ የአብይ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ::

በመድረኩም የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር በየነ ባራሳ, የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ የኮሚቴ አባላት የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::

በመድረኩም አጠቃላይ ክልላዊ የትራፊክ አደጋ መከላክያ የመነሻ ሠነድ በቢሮ ኃላፊ በአቶ ታምሩ ታፌ ቀርቦ የመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት በማድረግ በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ በማንሳት ሁሉም እንደ ተቋማቸው ወስደው የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ ገልፀዋል::

በተጨማሪም በክልል ደረጃ እንዲሁም በሁሉም ዞኖች እንዲሁም በወረዳዎች የግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስቷል::

የትራፊክ አደጋ እንዴ ሀገር እያደረሰ ያለዉን ዘርፈ ብዙ ጉዳትን ለመቀነስ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ እንዲሰሩ ለማድረግ ታቅዶ የተዘጋጀ መድረክ ሲሆን በአስከፍው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የሞት የአካል ጉዳት እንዲሁም በእኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ እያደረሰ ያለውን ቀውስን ለመቀነስ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ተገልፆዋል::

በመጨረሻም ክቡር ምክትል ፕረዝደንት እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በቀጣይ ከኮሚቴ ምስረ ታ ጀምሮ በክልል ደረጃ በሚሰሩ ስራዎች ላይ በቅርበት በቅንጅት በመሥራት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ የድርሻቸውን እንዲወጡ እና ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል::

ሰኔ 03/2016 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ

newz199

ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች የመጀመሪያውን ክልላዊ የሴክተር መ/ቤቶች ዉድድር አሸናፊ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ::

ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች የመጀመሪያውን ክልላዊ የሴክተር መ/ቤቶች ዉድድር አሸናፊ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ::

ኮከቦቹ በሀዋሳ ሰማይ ላይ ደመቁ::

የተቋማችንን ተልዕኮ ለማሳለጥና የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ በጋራ ለጋራ ስኬት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በአጠረ ጊዜ ዉስጥ በመገንባት በመንግሥት ተቋማት የእግር ኳስ የስፖርት ዉድድር ላይ ገና ከጅማሬዉ በሁለቱም ፆታ ያስመዘገብነዉ  ቻምፒዮንነት/ አሸናፊነት የዉስጥ የሴክተራችንን ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችንን ለይተን ጥንካሬያችንን ይበልጥ አጎልብተን ጉድለታችንን በፍጥነት አርመንና አካክሰን ለመሥፈንጠር ለጀመርነዉ ጉዞ የትክክለኛ እርምጃ  ማሳያ ዉጤት መሆኑን የተረዳንበት ሕያዉ ምስክር ነዉ።

በመሆኑም ይኸንን ድል በቀጣይ ሁሉም ዘርፎቻችን:ዳይሬክቶሬቶቻችን: ባለሙያዎቻችንና መላዉ መዋቅራችን በተሰጠን ቦታ ከተባበርን ከተደጋገፍን ከተቀናጀን ግልፀኝነትን ፈጥረን ሌብነትና ብልሹ አሠራር በተግባር ተፀይፈን ሕባችንን በፍትሃዊነትና በቅንነት በተሰጠን ጊዜ አገልግለን ዕርካታዉን ካረጋገጥን ሥራችንን በግልፅ መዝኖ የሚገባንን ዉጤት በሚሰጠንና በሚከፍለን እግ/ር: መንግሥት:ፓርቲና ሕዝባችን ፊት ገንዘብ ሊገዛዉ በማይችል ዋጋ የሚተመነዉን ምስክርነትና ሽልማት በአደባባይ ከመቀበል የሚበልጥ ክብርና ዕርካታ ምን አለ? የሴክተራችን ዕንቁና ተወዳጅ የሆናችሁ የማከብራችሁ ባልደረቦቼና  ቤተሰቦቼ ።

ስለዚህ ይህንን አዉቀን በቀሪ ጊዜያችን የአምላካችን የእግ/ር  ዕገዛና ብርታት ፀጋዉን ከሁሉም በላይ አብሮነቱ ጥበቃዉ በዝቶልን ከሚሰጠን ሰላምና አንድነት የሚመነጭ ፍቅር እና ርህራሄ ተላብሰን በዓላማ አንድነት ተጋምደን የሚጠበቅብንን የላቀ ዉጤት አስመዝግበን ለበለጠ ሽልማት እንድንነሳ አደራ እያልኩ ዉድና ዕንቁ የሆናችሁ ተጫዋቾቻችንና የሴክተራችን ሠራተኞች እንዲሁም መላዉ የስፖርቱ ቤተሰቦች ለድካማችሁ ድሉ ስለሚገባችሁ ኮርተንባችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን እላለሁ።

በመጨረሻም ፍፃሜያችን በድል ዋንጫ ታጅቦ በሀዋሳ ሰማይ ላይ ደስታችሁ እንደደመቀ በተሰማራችሁበት ሁሉ ጅማሬያችሁ ሂደታችሁና ፍፃሜያችሁ በአንድነት ለጋራ ድል በጠንካራ ቲሞ ስፕሪት በደስታ በስኬት በፍቅር በዉጤት በድርብ ድል የደመቀ ይሁንላችሁ ።

ብሩህ ጊዜ!

መጋቢት 22/2016 ዓ.ም.

ሐዋሳ, ሲዳማ

newz112

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ከመጋቢት 09 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለፀ::

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ከመጋቢት 09 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለፀ::

በመንገድ የትራፊከ አደጋ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለመቀነስ የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በሲዳማ ክልል ከመጋቢት 09 -መጋቢት እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ታምሩ ታፌ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ታምሩ ታፌ እንደተናገሩት በህጉ ዙሪያ ለተቆጣጣሪ አካላት እና ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር በማስተባበር፣በመደገፍ፣ በመከታተልና በመገምገም ህግ የማስከበር ስራው ተጠያቂነት ባለው መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ፤በሞተር ሳይክል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ስራ ማከናወን ፣ከክልል የዞንና ወረዳ ኃላፊዎች፣ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ፣ከትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እና በዋናነት ይህን አስከፊ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መቀነስ እንደሆነ በመግለጫቸው ገልፀዋል፡፡

የተቀናጀው የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስተባባሪነት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ ጋር በቅንጅት የሚሰራ ይሆናል፡፡

በፕሮግራሙም መሰረት ለአሽከርካሪዎች እና ለተማሪ ትራፊክ ክበብ ኮሚቴዎች የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሐዋሳ ከተማ, በይርጋአለም ከተማ እንዲሁም በአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር እንደሚሰጥ በመግለጫ ወቅት ተገልፆዋል::

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በሲዳማ ክልል ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እስከ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ዳዬ ድረስ በተመረጡ መስመሮች ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

መጋቢት 08/2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

newz49

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጥና የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጥና የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

ከክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ፤ከክልሉ ጠቅላይ  ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም በየደረጃው ካሉ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በክልላችን በተመረጡ ቦታዎች በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአሮጌው መናኸሪያ ውስጥ :- የሶስተኛ ወገን፣ የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ቦሎ፣ የስምሪት ሂደት ፣የተሳፋሪ የትኬት አቆራረጥና መውጫ አሰጣጥን አስመልከቶ እንዲሁም በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ መናኸሪያ ዉስጥ ቁጥጥር ተደርጓል:: የቁጥጥርና የተቀናጀ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን በቁጥጥር ወቅት ጎልተው የታዩ ደንብ ተላላፊዎች በህጉና በደንቡ መሠረት ተገቢው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ፡፡ 

የተቀናጀውን የቁጥጥር ቡድን በየደረጃው ሥራውን  ያለበት ሂደትና ያጋጠሙ ችግሮችን ከሁለቱም መዋቅር ጋር በመሆን ጎን ለጎን በመገምገም በቦታው እየተፈታ መሄድ እንዳለበትና  የቁጥጥር ተግባሩ አጠናክሮ በማስቀጠል የህግ ማስከበርና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል ።

የተቀናጀው የቁጥጥር ቡድን በቀጣይም በሌሎችም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚቀጥል ይሆናል ።

የካቲት 11 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ

bheadz2

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የቢሮው ስፖርት ቡድን የፋይናንስ አቻውን በማሸነፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ ::

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የቢሮው ስፖርት ቡድን የፋይናንስ አቻውን በማሸነፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ ::

የቢሮአችን ዕንቁዎች ዋጋችዉ በምንም የማይተመን ብርቅዬዎች ናችሁና ገና ከመነሻዉ በስፖርቱ ያስመዘገባችሁትን ድል በቀጣይም እስከፍፃሜዉ አስጠብቃችሁ ብቻ ሳይሆን የበለጠ እያስመዘገባችሁ እንደምትቀጥሉ እምነቴ ፅኑ ነዉ።

በስፖርቱ የተጀመረው ስኬታማነት በመንገድ ልማት፣ በትራንፖርት ዘርፍ፣ በመንገድ ደህንነትና በሰዉ ተኮር/ በጎ አገልግሎት ሥራዎቻችን ላይ የቢሮአችንን ተልዕኮ ማሳካት ብቻ ሳይሆን የልህቀት ማዕከል አድርገን ማየት ብለን ያስቀመጥነዉን ግብ ተባብረንና ተደጋግፈን የቡድን መንፈስ/team spirit/ ገንብተን ሕዝባችንን ዝቅ ብለን በማገልገል የተገልጋዮቻችንን ዕርካታ በማረጋገጥ ራዕያችንን ዕዉን እንደምናደርግ ለገባነዉ ቃል ኪዳን የማሳኪያ ማሳያ ዉጤት ስለሆነ እንኳን ደስ አለን።

የቀድሞ ቢሮዬ ባልደረቦቼ ሽንፈት መዉደቂያ ሳይሆን ለቀጣይ ስኬት ጉድለትን በመለየት የመፍትሄ አማራጭ በመፈተሽ የድል መንደርደርያ መንገድ ነዉና አይዟችሁ።

 ድልና ድምቀት ለጋራ ራዕያችን ለሁላችን ይሁን ።

newz94

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማጠቃለያ ተደረገ::

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማጠቃለያ ተደረገ::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ኃላፊ፣ ክቡር አቶ ዘገዬ ሀመሶ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ፣ የዞን ዋና አስተዳደሪዎ እና የፊት አመራሮች፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተደርጓል::

በሴክተር ጉባኤው ላይ የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሠነድ እንዲሁም የባለ ሁለት ጎማ ሞተር አደረጃጀት መመሪያ የጉባኤ አጀንዳዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጉባኤው ተሳታፊዎችም በቢሮ ደረጃ እስከ ታች እየተከናውኑ ያሉትን ተጨባጭ ለዉጥ እያስመዘገቡ የሚገኙ እንደሆነ አንስተው በተለይ ከመንገድ ልማት ሥራዎች አንፃር ከጥራት ጋር ተያይዞና በጊዜ ከማጠናቀቅ አንፃር ትኩረት ይበልጥ እንዲደረግ ተነስቷል::

በሌላም በኩል በመንገድ የትራፊክ አደጋ መከላከል ረገድ እየመጡ ያሉትን ለዉጦችን በማጠናከር የትራፊክ አደጋ እያስከተለ የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ በመቀናጀ መቀነስ እንደሚገባ ተገልፆዋል::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ በተነሱ ሃሳቦች ላይ ምላሽ በመስጠት በ ጋራ በመቀናጅት መሥራት ከቻልን በመጨረሻም የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልፆዎ በእለቱም ለሴክተር ጉባኤ መሳካት የራሳቸውን ሚና ለተወጡ አካላት የምስጋና እዉቅና ሰርትፊኬት ተሰጥተዉ የእለቱ መድረክ ማጠቃለያ ተደርጓል::

ጥር 17/2016 ዓ.ም

newz91

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ተጀመረ::

የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ እና የመንገድ ደህንነት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የንቅናቄ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ተጀመረ::

በመድረኩም የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ኃላፊ ፣ ክቡር አቶ ዘገዬ ሀመሶ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ፣ የዞን ዋና አስተዳደሪዎች እና የፊት አመራሮች፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳና አስተዳዳሪዎች፣ የፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል::

በሴክተር ጉባኤው ላይ የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት፥ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሠነድ እንዲሁም የባለ ሁለት ጎማ ሞተር አደረጃጀት መመሪያ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል::

ጥር 17 /2016 ዓ.ም

newz31

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የመንገድ ልማት ሥራዎች ያለበትን ደረጃ ገመገሙ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የመንገድ ልማት ሥራዎች ያለበትን ደረጃ ገመገሙ::

ግምገማ የተደረገው የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ በበጀት ዓመቱ በመንገዶች ባለስልጣን በኩል እና በገጠር ተደራሽ መንገድ በዩራፕ ዘርፍ ታቅዶ እየተገነቡ ያሉትንና የጥገና መንገዶች እንዲሁም የድልድይ ግንባታ ሥራዎች የግምገማዉ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እየተገመገመ ይገኛል::

በመድረኩም የርዕሰ መስተዳድር አማካሪዎች የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እና የማናጅመንት አባላት የአራቱም ዞን የፊት አመራሮች እንዲሁም የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የፅ/ቤት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል::

በግምገማዉም መድረክ ላይ በመንገዶች ባለስልጣንና በዩራፕ ዘርፍ የታቀዱና በ6 ወር ዉስጥ እስከ አሁን ያለው አፈፃፀምን በተመለከተ የተዘጋጀ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል::

በቀረበው የሪፖርት ሠነድ መነሻ የመድረኩ ተሳታፊዎች ከእቅድ አፈፃፀም አንፃር ያለውን ሁኔታ ከዞን እና ወረዳዎች ደረጃ እታች ያለውን ጉድለትና ጥንካሬ አንስቷው በቀጣይ ልስተካከሉ የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮችን በአራት ቡድን ተከፍሎ ጥልቀት ያለው ውይይት እየተደረገ ነው::

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቀጣይ ትኩረት የሚደረጉ በተለይ የዝናብ ወቅት ሳይገባ ቶሎ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅና ከመንገዶች ጥራት አንፃር በቢሮ ደረጃ ትኩረት ልሰጡ የሚገቡ ጉዳዮች ተለይቶ ውይይት በማደረግ ልፈቱ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የውይይት አቅጣጫ ተደርጓል::

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የተጀማመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑ አንስተዉ በቀጣይ ከጊዜ ጋር ተያይዞ የምታዩ ችግሮች መፈታት የሚገባቸውና ከመንገዶች ጥራትና እስታንዳርድ ረገድ የሚታዩ ጉድለቶች በተለያ ከግብአት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተስተዋሉት በፍጥነት መታረም ያለባቸው እንደሆነ አቅጣጫ ተቀምጦ ለመንገዶች ግንባታ ስራዎች ሁሉም አካላት መቀናጀት እንዳለባቸዉ ገልፆዎ የቡድን ውይይቱ በጥልቀት በዞን ማዕከል አመራር እየተመራ እየተደረገ ይገኛል::

ከቡድን ውይይት በመቀጠል በጋራ ቡድን ሪፖርት ቀርቦ ማጠቃለያ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል::

ጥር 9 /2016 ዓ.ም

ሐዋሳ, ሲዳማ