የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ በሰሜን ሲዳማ ዞን በለኩ ከተማ አስተዳደር በራማዳ ቀበሌ አቅም ለሌላቸዉ ቤተሰብ የቤት ግንንባታ ማስጀመሪያ ተካሄደ::


በፕሮግራሙም የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች የሰሜን ሲዳማ ዞን አመራር እንዲሁም የለኩ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት ለአንዲት አቅመ ደካማ እና 4 ልጆች ላሏት እናት ግንባታ የማስጀመር ስራ ተጀምሯል ::
ይሄ ተግባር የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች በራሳቸው ተነሳሽነት እና ፍላጎት ገንዘብ በማዋጣት ያስጀመሩት እንደሆነ ተገልጿል::
በመቀጠልም በለኩ ከተማ አስተዳደር የመናሃሪያ ግቢ ዉስጥ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መሪሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በቀጣይ መከታተል እና መንከባከብ ከሁሉም የሚጠበቅ እንደሆነ የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አስገንዝቧል::
የሰሜን ሲዳማ ዞን ተወካይ በበኩላቸዉ የሲዳማ ህዝብ ያለው ለሌለዉ የማካፈል የባህል እሴት ያለው መሆኑን ጠቅሶ ይሄን ተግባር በቢሮ ደረጃ ማከናወን በመቻሉ በዞኑ ስም ምስጋናቸዉን አቅርቧል::
በሌላም በኩል የለኩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፀጋዬ አባቴ መዕልክታቸዉን ሲያስተላልፉ ደሃን እና አቅም የሌላቸዉን መርዳት ፈጣሪ የምደሰትብን ተግባር በመሆኑ በቀጣይ መሰል ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል::
በመቀጠልም ከበጎ ተግባር ጎን ለጎን በለኩ ከተማ አስተዳደር ስለ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን ግ ንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል::
ሐዋሳ, ሲዳማ
መስከረም 10፣ 2016 ዓ.ም.
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::