የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ድንገተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ።

የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ድንገተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ።

በሲዳማ በሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጅስትክ ሚኒስቴር የመድህን ፈንድና የመንገድ ደህንነት አገልግሎት ባለሙያዎች እንዲሁም የፌደራል ፖልሲ ኮሚሽን ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ድንገተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ።

መጋቢት 1/2015 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ፣ በቱላ ክ/ከተማ ፣ እንዲሁም ከሀዌላ ወረዳ እስከ ሸበድኖ ወረዳ ሞሮቾ ከተማ ድረስ የትራፊክ አደጋ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫና ድንገተኛ ቁጥጥር ሥራ በሁለተኛ ቀን ፕሮግራም ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የዚህ የድንገተኛ የተቀናጀ ቁጥጥር ዋና አላማው አሽከርካሪዎች ከመጠን በላይ እንዳያሽከረክሩ፣ ከወንበር ቁጥር በላይ ትርፍ ሰዉ እንዳይጭኑ ትምህርት በመሰጠትና ደንብ ተላልፎ የተገኙ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ::

በሌላም በኩል በድንገተኛ ቁጥጥር ወቅት ሰሌዳ, ቦሎ ፣የሦስተኛው ወገን ፣ የብቃት ማረጋገጫና በሌሎች ጉዳዩች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን የጀመረው የተቀናጀ የቁጥጥር የሁሉም በሲዳማ ክልል ውስጥ ባሉት ወረዳዎች ላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ታዉቋል ::

…………………………………………….

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Comments are closed.