የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ ::

የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ ::

የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም የሶስተኛ ቀን ፕሮግራም በቦርቻ ወረዳ በይርባ ከተማ እና በአለታ ጩኮ ወረዳ በጩኮ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ ::

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀ “የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ቃል የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ዘሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል :::

የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በቀን 17/04/2015 አ. ም መነሻውን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በማድረግ በቦርቻ ወረዳ አስተዳደር አከባቢ እና በይርባ ከተማ,በአለታ ጩኮ ወረዳ አስተዳደር አከባቢ እና በአለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደር የመንገድ የትራፊክ አደጋ መከላከያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር እና ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የመን/ልማ/እና ትራ ፅ/ቤት ባለሙያዎች እና የፖሊስ ፅ/ቤት አካላት በጋራ በመቀናጀት ግንዛቤ ተሰጥቷል :

በአለታ ጩኮ ወረዳ አከባቢ እና በአለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደር በተሰራ ሥራ ተስፋ ሰጪ ለዉጦች እየመጡ ያሉ ቢሆን ባለ ሁለት ጎማ ሞተር ከልክ በላይ በመጫን እያደረሱ ያሉትን አደጋ በተቀናጀ መልኩ በመከላከል ማስቆም እንደሚገባ ለማየት ትችሏል ::

የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙም በቀጣይ ጊዜያት በሁለተኛ ዙር በተመሳሳይ ሁኔታ በተመረጡ ከተሞችና ወረዳዎች የሚቀጥል እንደሆነ ተጠቅሷል ::

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Comments are closed.