በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።

የቢሯችን አመራርና ሠራተኞች በጋራ በመሆን በዓለም ለ37 ጊዜና በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤችአይቪ/ኤድስን ቀን ” ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤችአይቪ/ኤድስ አገልግሎት ለሁሉም ” በሚል መሪ ቃልና እንዲሁም በዓለም ለ33ኛ ጊዜ ና በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀንን “የሴት ልጅ ጥቃት የኔም ነው ስለዚህ ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በጥምረት አክብረዋል።

መድረኩን የከፈቱት የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኮረኔል ሮዳሞ ኪአ በመልዕክታቸው:- የዛሬው ቀንን ስናከብር ኤችአይቪ/ኤድስና በሴቶችና ህፃናት ፆታዊ ጥቃት የሀገራችንና የዓለም ችግር ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ስለሆነም ሁላችንም ቆም ብለን እራችንን በመመልከት የመከላከል ሀላፊነትና ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


በክልሉ ጤና ቢሮ የኤችአይቪ/ኤድስ ሜንስቲሚንግ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት አሸናፊና በክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ የሥርዓተ – ፆታ ሜኒስቲሪሚንግ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት በቀለ አሁናዊ ሆኑ መረጃዎችን የሚያሳዩ ሰነዶችን አቅርበዋል።
በቀረቡት ሠነዶች ላይ አቅራቢዎቹ ያላቸውን ከፍተኛ ልምድና ብቃት በመጠቀም የበሽታውን ስርጭትና መስፋፋት እንዲሁም እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ትንኮሳ መድረኩን ባሳተፈ ውይይት በሳል ግንዛቤ ማስጨበጥ ችለዋል።


ከፍተኛ ባለሙያዎቹም ለተሳታፊዎች ይህ ችግር በሁላችችንም ቤት ሊከሰት የሚችል መሆኑን በመገንዘብ የዜግነት ግዴታና ሀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው የሚገኙ ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰብም የበሽታውን አስከፊነት በአካል ተገኝተው እንዴት መከላከል እንደሚቻል ተሞክሮአቸውን አስገንዝበዋል።

ተሳታፊዎች በመድረኩ ደስተኛ እንደሆኑና ወቅታዊ መረጃን በማግኘታቸው በመጠንቀቅ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠው መድረኩ ተጠናቋል።
ታህሳስ 2 ፣ 2017 ዓ.ም
ሐዋሳ፣ ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::