ወቅቱን የጠበቀ የሙያ ላይ ሥልጠና ግንዛቤን የማሳደግ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀዉ ለአሽከርካሪዎች በሥነ- ምግባር፣ አዲስ በተሻሻሉ የመንገድ ደህንነት ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም የመድህን ፈንድ አዋጆችን ለማሳወቅ በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ነው።
በመድረኩ በርካታ አሽከርካሪዎች፣ የትራፊክ ፖሊስ አባላት፣ የክልልና መምሪያ አመራርና ባለሙያዎች ተሣታፊ ሆነዋል።


የቢሮ ሀላፊ ተወካይና የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ ኮ/ ሮዳሞ ኪአ በመልዕክታቸው እንደገለፁት የዛሬው መድረክ ዓላማ አሽከርካሪዎች የተከበረ ሙያ ያላችሁ የተከበረውን የሰው ልጅን ህይወት ይዛችሁ የምትንቀሳቀሱ፣ በስነምግባር የታነፃችሁና አዳዲስ ከወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር እንድትተዋወቁ ታሳቢ በማድረግ ነው።
አክለዉም ባለፈው ዓመት በተከሰተው የትራፊክ አደጋ ዋናው መንስዔ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑን ገልፀው በዝግታና በእርጋታ እንድታሽከረክሩ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሰነዶች ቀርበው በሳል ሙያዊ ገለፃ ተደርጎባቸዋል።


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አዳነ አየለና የክልሉ መንገድ ደህ/አቅ/ግን/ድህ /አደ/መድህን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዶካ ከመድረክ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተውባቸው መግባባት ላይ ተደርሶ መድረኩ ተጠናቋል።
“በትራፊክ አደጋ አንድም ህይወት እንዳይጠፋ፣ አካል እንዳይጎድል፣ ንብረት እንዳይወድም ሁላችንም ሀላፊነት አለብን! “
መስከረም 2017 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::