ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች የመጀመሪያውን ክልላዊ የሴክተር መ/ቤቶች ዉድድር አሸናፊ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ::

ኮከቦቹ በሀዋሳ ሰማይ ላይ ደመቁ::
የተቋማችንን ተልዕኮ ለማሳለጥና የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ በጋራ ለጋራ ስኬት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በአጠረ ጊዜ ዉስጥ በመገንባት በመንግሥት ተቋማት የእግር ኳስ የስፖርት ዉድድር ላይ ገና ከጅማሬዉ በሁለቱም ፆታ ያስመዘገብነዉ ቻምፒዮንነት/ አሸናፊነት የዉስጥ የሴክተራችንን ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችንን ለይተን ጥንካሬያችንን ይበልጥ አጎልብተን ጉድለታችንን በፍጥነት አርመንና አካክሰን ለመሥፈንጠር ለጀመርነዉ ጉዞ የትክክለኛ እርምጃ ማሳያ ዉጤት መሆኑን የተረዳንበት ሕያዉ ምስክር ነዉ።


በመሆኑም ይኸንን ድል በቀጣይ ሁሉም ዘርፎቻችን:ዳይሬክቶሬቶቻችን: ባለሙያዎቻችንና መላዉ መዋቅራችን በተሰጠን ቦታ ከተባበርን ከተደጋገፍን ከተቀናጀን ግልፀኝነትን ፈጥረን ሌብነትና ብልሹ አሠራር በተግባር ተፀይፈን ሕባችንን በፍትሃዊነትና በቅንነት በተሰጠን ጊዜ አገልግለን ዕርካታዉን ካረጋገጥን ሥራችንን በግልፅ መዝኖ የሚገባንን ዉጤት በሚሰጠንና በሚከፍለን እግ/ር: መንግሥት:ፓርቲና ሕዝባችን ፊት ገንዘብ ሊገዛዉ በማይችል ዋጋ የሚተመነዉን ምስክርነትና ሽልማት በአደባባይ ከመቀበል የሚበልጥ ክብርና ዕርካታ ምን አለ? የሴክተራችን ዕንቁና ተወዳጅ የሆናችሁ የማከብራችሁ ባልደረቦቼና ቤተሰቦቼ ።
ስለዚህ ይህንን አዉቀን በቀሪ ጊዜያችን የአምላካችን የእግ/ር ዕገዛና ብርታት ፀጋዉን ከሁሉም በላይ አብሮነቱ ጥበቃዉ በዝቶልን ከሚሰጠን ሰላምና አንድነት የሚመነጭ ፍቅር እና ርህራሄ ተላብሰን በዓላማ አንድነት ተጋምደን የሚጠበቅብንን የላቀ ዉጤት አስመዝግበን ለበለጠ ሽልማት እንድንነሳ አደራ እያልኩ ዉድና ዕንቁ የሆናችሁ ተጫዋቾቻችንና የሴክተራችን ሠራተኞች እንዲሁም መላዉ የስፖርቱ ቤተሰቦች ለድካማችሁ ድሉ ስለሚገባችሁ ኮርተንባችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን እላለሁ።


በመጨረሻም ፍፃሜያችን በድል ዋንጫ ታጅቦ በሀዋሳ ሰማይ ላይ ደስታችሁ እንደደመቀ በተሰማራችሁበት ሁሉ ጅማሬያችሁ ሂደታችሁና ፍፃሜያችሁ በአንድነት ለጋራ ድል በጠንካራ ቲሞ ስፕሪት በደስታ በስኬት በፍቅር በዉጤት በድርብ ድል የደመቀ ይሁንላችሁ ።
ብሩህ ጊዜ!
መጋቢት 22/2016 ዓ.ም.
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::