የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ከመጋቢት 09 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለፀ::

በመንገድ የትራፊከ አደጋ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለመቀነስ የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በሲዳማ ክልል ከመጋቢት 09 -መጋቢት እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ታምሩ ታፌ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ታምሩ ታፌ እንደተናገሩት በህጉ ዙሪያ ለተቆጣጣሪ አካላት እና ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር በማስተባበር፣በመደገፍ፣ በመከታተልና በመገምገም ህግ የማስከበር ስራው ተጠያቂነት ባለው መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ፤በሞተር ሳይክል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ስራ ማከናወን ፣ከክልል የዞንና ወረዳ ኃላፊዎች፣ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ፣ከትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እና በዋናነት ይህን አስከፊ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መቀነስ እንደሆነ በመግለጫቸው ገልፀዋል፡፡


የተቀናጀው የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስተባባሪነት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ ጋር በቅንጅት የሚሰራ ይሆናል፡፡
በፕሮግራሙም መሰረት ለአሽከርካሪዎች እና ለተማሪ ትራፊክ ክበብ ኮሚቴዎች የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሐዋሳ ከተማ, በይርጋአለም ከተማ እንዲሁም በአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር እንደሚሰጥ በመግለጫ ወቅት ተገልፆዋል::


የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራ በሲዳማ ክልል ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እስከ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ዳዬ ድረስ በተመረጡ መስመሮች ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡
መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
ሐዋሳ, ሲዳማ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::