በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
በምክክር መድረኩ በዞን ደረጃ እየተሰሩ የሚገኘው የግንባታ እና ጥገና መንገዶች እንዲሁም የድልድይና እስትራክቸር ስራዎች አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ተገምግሟል::
ኮንትራክተሮቹ ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች ከተቀረፈላቸው ፕሮጀክቶቹን በተባለው ጊዜ ዉስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል::
የፕሮጀክቶች አፈፃፀም በጥራት አጠናቆ ከማስረከብ አንፃር የሚታዩ ችግሮች ; የኮንትራክተሮች የአፈፃፀም ፍጥነት ጊዜን ታሳቢ በማድረግ ከመስራት ረገድ የሚታዩ ችግሮች በቀጣይ ልታረሙ የሚገቡ እንደሆኑ ተገምግሟል::
የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ኖኦራ በመድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት :- በዞን ደረጃ በቢሮ በኩል መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ እንዲሰራ እያደረገ በመሆኑ ከአቅርቦት ጋር የሚታዩ ችግሮችን ለመንገድ እና ድልድይ መሰረተ ልማት ቅድሚያ እንዲሰጥ ለማድረግ ርብርብ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል::
በቢሮ በኩል የተጀመረው የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በማድረግ ፕሮጀቶች በጥራት እንዲሰሩ ማድረግ የሚገባዉ እንደሆነ የቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል ::
ኮንትራክተሮች ዉል በገቡት መነሻ በማጠናቀቅ ለአከባቢ ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንፃር ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው የቢሮ ኃላፊ ጨምሮ ተናግረዋል::
በመጨረሻም በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቢሮ ኃላፊ በዞኑ የተያዙ እና እየተሰሩ ያሉትን ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ መልኩ በማከናወን ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ በማድረግ ሕብረተሰብን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::
በመጨረሻም በቢሮ በኩል ጠንካራ የክትትል እና ግምገማ ስርዓት የተዘረጋ በመሆኑ በፕሮጀክት ሳይት ደረጃ የሚታዩ ችግሮች እየተፈቱ እንዲሄዱ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል:
በግምገማ መድረኩ የቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ; የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ኖኦራ ; የተጠሪ ተቋም አመራርና ባለሙያዎች; የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የመምሪያ አመራሮች እንዲሁም ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች ተገኝተዋል::
=======================
የካቲት, 19/2018 ዓ.ም
በንሳ, ዳዬ




