የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
በሲዳማ ክልል የመናኸሪያዎች አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ በመደረጉ አገልግሎቱን ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራዉ የጉብኝት ቡድን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ እና በአሮጌ መናኃሪያዎች ተገኝተዉ የአገልግሎት አሰጣጡን ሂደት ምልክታ አድርገዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጡ ሂደት የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ቢሮዉ በክልሉ የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርትን መመሪያ በማዘጋጀት ተግባራዊ እያደረገ በመሆኑ በትራንስፖርት በኩል የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ በምልክታ ወቅት ተጠቅሷል፡፡
በወጣቶች የተደራጁ ማህበራት ሁሉም የቢሮ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እጣ በማንሳት ከቢሮው ጋር ዉል ገብተው ወደ ስራ ከገቡ ወዲህ ያለው የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የተቀመጡ ተግባራትን መነሻ በማድረግ እየተሰሩ ያሉበትን ሁኔታ የቢሮ ማናጅመንት አመራሮች ጎብኝተዋል፡፡
በሁለቱም መናኃሪያዎች ዉስጥ የተገልጋይ ማረፊያዎች፤የመጸዳጃ ቦታዎች እንዲሁም ለተገለጋይ ትኬት የሚሰጥበት አከባቢ ይበልጥ እንዲለማ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባቸው ተብራርቷል፡፡
የተሸከርካሪዎች መግቢያ እና መዉጫ፤የዲጂታል ሚዛን፤ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዲስፕለይ ማድረጊያ እስክሪኖች እንዲሁም በካሜራ የታገዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት የተደራጁ ማህበራት ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሆነ መመልከት ተችለዋል፡፡
በሌላም በኩል ከትራፊክ ፖሊሰ እና ከመናኃሪዎች አስተባባሪዎች ጋር በቅንጅት በመስራት አገልግሎቱን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿዋል፡፡
የተደራጁ ወጣቶች የሲና ሀርድ እንዲሁም የስታር ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ማህበራት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም የእዉቀት ሸግግር በማድረግ ወጣቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርትን ተግባራዊ ለማደረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች ዉጤቶች እየታበት በመሆኑ በቀጣይም በመመሪያዉ ዉስጥ የተካተቱ አገልግሎቶች በሙሉ እንዲጀመሩ በቅርበት ድጋፍ ክትትል እንደሚደረግ የቢሮ ሃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ የቢሮ አመራሮች፤የሀዋሳ ከተማ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች ተገኝተዉ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
=====================
የመንግስት ኮሙኒኬሸን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ጥር/2018 ዓ.ም
ሀዋሳ፥ሲዳማ




