የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
ሴክተሩ በገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና (RCFSP) ፕሮግራም አማካይነት የተለገሱ 7 ያማሀ ሞተር ሳይክሎችን በፕሮጀክቱ ለሚደገፋ 7 ወረዳዎች የርክክብ መርሀ- ግብር አከናውኗል:: የቢሮ ሀላፊው አቶ ጎሳዬ ጎዳና ለወረዳ ፅ/ቤት ሀላፊዎች የቁልፍ ርክክብ ሥነ- ሥርዓት ሲያደርጉ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል::
ይህ በፕሮጀክቱ አማካይነት ከፌዴራል መንግስት ያገኘናቸው 2 ሀርድ ቶፕ መኪናዎች፣ 7 ሞተር ሳይክሎች የ100 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀምን ግብረ- መልስ እየሰጠን ባለንበት ወቅት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል::
የፕሮጀክቱ ድጋፍ የመንገድ ልማት ተግባራችንን የበለጠ ቀልጣፋና የተሳለጠ ያደርገዋል ሲሉ አብራርተዋል::
በመሆኑም እነዚህ የተለገሱ ተሽከርካሪዎች በወረዳዎች የሚሰሩትን መንገዶች በቅርበት ለመደገፍና ለመከታተል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ::
ከዚህ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ ጠንክራችሁ ከሰራችሁ ለመንገድ ሥራ የሚውሉ ማሽነሪዎችን እንደሚሰጡን ቃል መግባታቸውን አስረድተዋል::
የወረዳ ፅ/ቤት ሀላፊዎችም ኮንትራክተሮች የመንገድ ሥራውን ሲያከናውኑ ለሚገጥማቸው እንደ ነዳጅ ያሉ የዕጥረት ተግዳሮቶችን ከሚመለከታቸው የዞን አመራር ጋር በመቀናጀት መፍትሄ በማበጀት ልትደግፉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል::
በመጨረሻም እነዚህን ሞተር ሳይክሎች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ በማዋል ልማቱን በማሳለጥና በአግባቡ በመጠቀም ልትገለገሉ ይገባል ሲሉ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል::
ታህሳስ – 27/ 2018 ዓ.ም
ሀዋሳ
Muli Yanna Odoo
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ ::
በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል::
የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ::
የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው::
Sidaamu qoqqowi doogote ijaari loosi kaajje sufasi xawinsi