ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::

ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::

p

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ የጉብኝት ቡድን በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን መነሻውን በማድረግ በወረዳዎች እየተሰሩ የሚገኙ የመንገድ ግንባታዎችን እና በሕብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎችን ምልከታ አድርገዋል ::

በምልከታቸውም በፌዴራል የመንገዶች አስተዳደር በኩል ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የአስፓልት መንገድ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል::

የመንገዱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ዉስጥ ከማከናወን አንፃር ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮች ተቀርፈው በጥሩ ሁኔታ ግንባታው መከናወን መጀመሩ እጅግ አበራታች እንደሆነ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል::

በሌላም በኩል በክልሉ መንግስት በመንገዶች ባለስልጣን እና በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸው እየተከናወኑ የሚገኙ መንገዶችን የጥገናና ግንባታ ሂደቶች ያሉበት ሁኔታ ምልከታ ተደርጓል::

በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ግንባታው እየተከናወ የሚገኘው የቦካሶ ዳዋሌ የ16 ኪሜ የመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክት ያለበት ደረጃ መመልከት ተችሏል::

የመንገዱ ግንባታ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በማድረግ ለአከባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ብዙ አስተዋፆ ያለው በመሆኑ በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተብራርቷል::

በተጨማሪም በሕብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉት የመንገድ ከፈታ ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች ላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል ::

በክልሉ በመንግስት በጀት ብቻ የመንገድ ግንባታን በማከናውን ሁሉንም ማህበረሰብ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተደራሽ  ማድረግ ስለማይቻል በሁሉም ዞኖች አመራሩ ትኩረት በመስጠት ሕዝቡን በማስተባበር የመንገድ ከፈታ እና የገጠር ኮሪደር ሥራዎችን መስራት እንደሚገባቸው ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምሮ ገልጸዋል ::

የቢሮው ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ በበኩላቸው በክልል ደረጃ በቢሮ በኩል እየተሰሩ ያሉት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እና ጥራት እንዲጠናቀቁ ከሁሉም የባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ህዝባችን ተጠቃሚ እንዲሆን እንሰራለን በማለት ተናግረዋል::

በጉብኝቱም የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አብርሃም ማርሻሎ የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞን አመራሮች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል ::

በቀጣይ በሌሎች ዞኖች የጉብኝት ፕሮግራሙ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል::

Tenne Odoo Iillishshe

Comments are closed.