በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::

ከፌዴራል መንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ከመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ የተውጣጣ ግብረ ሀይል የድጋፍና ቁጥጥር ሥምሪት እንደተሰጠው ተመላከተ።

የድጋፍና ቁጥጥር ተልዕኮው የሚተገበረው በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማና በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ሲሆን ለ12 ቀናት እንደሚቆይም ተብራርቷል።

የቢሮ ሀላፊው አቶ ታምሩ ታፌ ሥምሪቱን ለግብረ- ሀይሉ ሲሰጡ በንግግራቸው:- ተልዕኳችሁ በዋናነት በመናኽሪያዎች አካባቢ የሚካሄድ የህግና ደንብ ትግበራ በተጨማሪም በእንቅስቃሴ ወቅት አሽከርካሪዎች ደንብና ህግ ጠብቀው ስለመንቀሳቀሳቸው ትኩረት ሠጥተው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

አክለውም ተልዕኳችሁ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ተቋማችን ከጎናችሁ ነው ሲሉ አብሮነታቸውን አረጋግጠዋል።
ለተቀናጀ ቁጥጥር ሥራ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲንቀሳቀሱ እና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስቧል::

የከተማ ታክሲ ታሪፍ ጥናት ተሰርቶ በሀዋሳ እና በክልል ከተሞች ተግባራዊ እንዲደረግ በቢሮ በኩል የወረዳውን ተግባራዊነቱ በግብረ ኃይሉ በኩል በትኩረት ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ ጨምሮ አስገንዝቧል::
18/03/2017 ዓ.ም.
ሐዋሳ ሲዳማ
Muli Yanna Odoo
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::