ተቀናጅቶ መሥራት ለሴክተር ሥራ መሳካት ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ::

በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ ተካሂዷል::
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ አስፋው ጎኔሶ እንደገለፁት ይህ ሴክተር ለሲዳማ ሕዝብ የመልማት ቁጥር አንድ አጀንዳ የሆነውን የመንገድ የልማት ሥራን የሚሰራ ተቋም በመሆኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል::
የመንገድ እና የድልድይ ግንባታ ተደራሽነት እንደ ጥሩ የሚታይ ቢሆንም ከጥራት ጋር ተያይዞ ለሚታዩ ችግሮች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ተገልጿል::

በሌላም በኩል የትራንስፖርት ዘርፍ አከባቢ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ የሕዝቡን እንግልት ማስቀረት እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራዎችን ሪፎርም በማድረግ የሚታዩ ችግሮች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይገባል በማለት ተናግሯል::
በመክፈቻው ወቅት የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታምሩ ታፌ እንደተናገሩት በቢሮ ደረጃ በመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራዎች በበጀት ዓመቱ ዉጤታማ እንደነበረ ተናግረዋል::
በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ዘርፍም በተሰራው ሥራ የሞት መጠን የቀነሰ ቢሆንም በሰው እና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ማስቆም እስካልቻልን ድረስ በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ ተጠቅሷል::
በክልል ደረጃ በ2016 በጀት ዓመት 107 የሞት አደጋ መከሰቱንና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እና የአካል ጉዳት የደረሰ በመሆኑ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በሙሉ በመቀናጀት የአደጋ መንስኤን በመለየት መስራትና መከላከል እንደሚገባ ተገልጿል::

በሴክተር ጉባኤው ለዉይይት መነሻ የሆኑ ሰነዶች የ2016 በጀት ዓመት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድን የቢሮው የልማት እቅድ በጀት ክትትል ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ወገኔ ታምራት ያቀረቡ ሲሆን የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከያ የንቅናቄ ሠነድን ኮሮኔል ሮዳሞ ኪአ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ዘርፍ ኃላፊ አቅርበው ውይይት ተደርጓል::

የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል እና አደጋዉን ለመቀነስ ሁሉም የባለድርሻ ተቋማት እና አካላት በመቀናጀት ከሰሩ የንቅናቄ ሠነዱን ሲያቀርቡ ኮሮኔል ሮዳሞ ኪአ ተናግረዋል::
በመድረኩም የተሻሻለው የትራፊክ ቅጣት ደንብ እና በአደጋ ወቅት የመጀመሪያ ሕክምና ክፍያ ማሻሽያ የተደረገውን ደንብ እስከታች በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በቀረበው ሠነድ ተብራርቷል::

በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ላይ ከተሳታፊ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥተው በቀጣይ በሴከተር ደረጃ በቅንጅት በመስራት የተጣሉ ግቦችን ማሳካት አስፈላግ መሆኑን ገልፆዎ ከዞኖች እና ከሐዋሳ ከተማ አስተዳር ጋር በቀጣይ በምሰሩ አቅጣጫዎች ላይ የግቢ ስምምነት ተደርጎ የሴክተር ጉባኤ መድረክ ማጠቃለያ ተደርጓል::
በመድረኩም የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አስፋው ጎኔሶ፣የቢሮ ኃላፊ ክቡር ታምሩ ታፌ፣ የፕሬዘደንቱ የመሰረተ ልማት አማካሪ ክቡር ዘገዬ ሀሜሶ፣ ክብርት ምንትዋብ ገ/መስቀል የከተማ እና መሰረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የዞንና የሐዋሳ ከተማ አመራሮች፣የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የባለድርሻ አካላት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::
=======================
መስከረም, 2017 ዓ.ም
Hawaasa, Sidaama
Muli Yanna Odoo
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በጋራ በተገኙበት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ::
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ::
በመዘናጋት ሥርጭቱ እየተዛመተ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስንና በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሏል ::
በሲዳማ ክልል ሀገራዊ የተቀናጀ መንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ተጀመረ ::